የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በልብ ህመም ሆስፒታል ገብተዋ የሚለውን ዘገባ ውድቅ አደረጉ
ላቭሮቭ "የምዕራባውያን ጋዜጠኞች እውነተኞች መሆን አለባቸው" ሲሉ መክረዋል

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ "ዘገባው የውሸት ጥግ የሚያሳይ ነው" ነው ብለውታል
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “ላቭሮቭ በልብ ህመም ሆስፒታል ገብተዋል” የሚለውን የአሶሺየትድ ፕሬስ ዘገባ ውድቅ አደረጉ።
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የምዕራባውያን ጋዜጠኞችን የውሸት ዘገባ ነው ሲሉም ወቅሰዋል።
አሶሺየትድ ፕሬስ ላቭሮቭ ወደ ባሊ ደሴት ለቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ከደረሱ በኋላ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ሲል የኢንዶኔዥያ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ከሰአታት በፊት መዘገቡ አይዘነጋም።
የ72 ዓመቱ የሩሲያው ከፍተኛ ዲፕሎማት ላቭሮቭ ለልብ ህመም ህክምና ተደርጎላቸዋልም ነበር ያለው ዘገባው።
ስለተሰራጨው ዜና የተጠየቁት ላቭሮቭ ምዕራባውያን ጋዜጠኞች የ70 አመቱ ፑቲን ታመዋል ብለው በውሸት ለአስር አመታት ሲጽፉ ቆይተዋል እናም የሚገርም አይደለም የሚል አስገራሚ ምላሽ ሰጥተዋል።
"ይህ በፖለቲካ ውስጥ አዲስ ያልሆነ ጨዋታ ነው" ሲሉም አክለዋል ላቭሮቭ ፈ በአስቂኝ ፈገግታ በተሞላበት አኳሃን።
"የምዕራባውያን ጋዜጠኞች እውነተኞች መሆን አለባቸው ፤ እውነትን መጻፍ አለባቸው" በማለትም ምክር አዘል አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል።
በዘገባው የተበሳጩት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በበኩላቸው "ይህ በእርግጥ የውሸት ጥግ የሚያሳይ ነው" ነው ብለውታል።
እንደሚባለው የሀሰት ዜና ሳይሆን ላቭሮቭ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
የላቭሮቭ ከቤት ውጭ በአንድ በረንዳ ላይ ተቀምጠው ቁምጣ እና ቲሸርት ለብሰው ሰነዶችን ሲያነቡ የሚያሳይ ቪዲዮም ለጥፏል ቃል አቀባይዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በነገው እለት በኢንዶኔዢያ በሚካሄደው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ አልገኝም ማለታቸው ተከትሎ ሩሲያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሰርገይ ላቭሮቭ መወከሏ የሚታወቅ ነው።