የሶማሊያ ጦር በሰነዘረው የተቀናጀ ጥቃት ቢያንስ 23 የአል-ሻባብ ታጣቂዎች ተገደሉ
የሶማሊያ ጦር በቅርቡ በሰነዘረው ወታደራዊ ጥቃት ቢያንስ 100 የአል-ሻባብ ታዋጊዎች መግደሉ አይዘነጋም
የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አዛዥ፤ አሸባሪዎቹ ከሶማሊያ ምድር እስካልተወገዱ ድረስ ዘመቻው ይቀጥላል ብለዋል
የሶማሊያ ጦር በሰነዘረው የተቀናጀ ጥቃት ቢያንስ 23 የአል-ሻባብ ታጣቂዎች ተገደሉ
የሶማሌ ብጦር በታችኛው ሸበሌ ክልል ሻላንቦድ አውራጃ አቅራቢያ በሚገኘው ዳኖዌ አካባቢ ባካሄደው የተቀናጀ ወታደራዊ ዘመቻ በትንሹ 23 የአልሸባብ ታጣቂዎች ሲገደሉ ሌሎች ቆስለዋል።
የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አዛዥ ጄኔራል ኦዶዋ ዩሱፍ ራጌ ብሄራዊ ጦሩ እና አፍሪካ ህብረት ሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ (አትሚስ) ኃይሎች፤ በአካባቢው ከአሸባሪዎች የተሰነዘረውን ጥቃት አድፍጠው በማክሸፍ በጋራ ኃይሎች ላይ ጉዳት ለማድረስ ያሰቡትን አሸባሪዎች ላይ መልሰው ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰዋል ብለዋል፡፡
የጦር አዛዡ “የእኛ ጦር ዛሬ ጠዋት በታችኛው ሸበሌ ክልል ዳኖው በተባለ ቦታ 23 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገድሎ ሌሎችን አቁስለዋል፤ ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሳሪያ ወስደዋል” ሲሉ መናገራቸውም ነው የሶማሌ ብሄራዊ ኤጀንሲ የዘገበው፡፡
አሸባሪዎቹ ከክልሉ እና ከመላ ሀገሪቱ እስካልተወገዱ ድረስ ዘመቻው ይቀጥላል ሲሉም ዝተዋል፡፡
ይህ ብእንዲህ እንዳለ በሂራን ክልል የአልሸባብ ታጣቂዎች በሃልጋን አውራጃ በመኪና ላይ ባደረሱት የአጥፎ ጠፊ የቦንብ ጥቃት አንድ ወታደር ሲገድል 12 ሌሎች ሲቪሎችም ቆስለዋል።
የሶማሊያ ጦር ከአንድ ወር በፊት በተመሳሳይ አከባቢ በሰነዘረው ወታደራዊ ጥቃት ቢያንስ 100 የአል-ሻባብ ታዋጊዎች መግደሉ አይዘነጋም፡፡
የሶማሌ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ከነሀሴ ወር ጀምሮ በአሜሪካ ድጋፍ የተቀናጀ ወታደራዊ ጥቃት መክፈታቸውታቸውን ተከትሎ አል-ሻባብ ከፍተኛ ጫና እየደረሰበት መሆኑ ይነገራል፡፡
የቀጣናው ስጋት የሆነው አሸባሪ ቡድን ለማጥፋት እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ የሽብር ቡድኑ መስራች የነበረው አብዱላሂ ናድር የተገደለበትም ጭምር መሆኑ ይታወቃል፡፡