በአውሮፕላን አደጋ ምክንያት ተዘግቶ የነበረው የሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ አገልግሎት መመለሱ ተገለፀ
ኢጋድ የሶማሊያ የእሳት አደጋ ሰረተኞች አደጋውን የተቆጣጠሩበትን ፍጥንት አድንቋል
በሶማሊያ የመንገደኞች አውሮፕላን በማረፍ እያለ ባጋጠመው አደጋ መገልበጡ ይታወሳል
በሶማሊያ በትናትናው እለት በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ ምክንያት ግልግሎቱ ተቋርጦ የነበረው የሞቃዲሾ አውሮፕላን መረፊያ ተመልሶ መከፈቱ ተገለፀ።
የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እንዳስታወቀው የአውሮፕላን ማረፊያው አደጋው ከደረሰ ከሁለት ሰዓት በኋላ ተመልሶ ተከፍቷል።
አደጋው በደረሰበት ሰዓት በሞቃዲሾ አዳን አዴ አውሮፕላን ማረፊያ ሊያርፉ የነበሩ አውሮፕላኖች ወደ ባይዶዋ ዞረው እንዲያርፉ ተደርጎ የነበረ ሲሆን፤ አንድ የኳታር አየር መንገድ አውሮፕላን ደግሞ በጂቡቲ እንዲያርፍ ተደርጎ ነበር።
በተያያዘ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሶማሊያ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ለአደጋው ለሰጡት ፈጣን ምላሽ አድናቆቱን ገልጿል።
የሶማሊያ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በአዳን አዴ የአውሮፕላን ማረፊያ የደረሰውን አደጋ ተከትሎም የሰው ህይወትን ለማዳን ለሰሩት ስራ ምስጋና ይገባቸዋልም ብሏል።
በትናትናው እለት በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በማረፍ ላይ የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበት ይታወሳል።
አደጋው ያጠመው የሀገር ውስጥ መንገደኞችን በማጓጓዝ ላይ የነበረ አውሮፕላን ሲሆን 33 መንገደኞችን ከባይደዋ ወደ ሀገሪቱ መዲና ሞቃዲሾ በማጓጓዝ ላይ ነበር፡፡
ይህ የመንገደኞች አውሮፕላን በሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ በማረፍ ላይ ሳለ ባጋጠመው ግጭት ምክንያት የተገለበጠ ሲሆን በሁሉም ተሳፋሪዎች ላይ ያጋጠመ የጎላ ጉዳት እንደሌለ የሶማሊያ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
አውሮፕላኑ ጁባ አየር መንገድ እንደሚባል የተገለጸ ሲሆን ስለ አውሮፕላኑ አደጋ መንስኤ እስካሁን ምንም የወጣ መረጃ የለም፡፡