ፕሬዝዳንት ሙሴ ባሂ የሶማሊያ መሪዎችን የሶማሊላንድን የስኬቶችን ከማስቶጓጎል እንዲቆጠቡ አሳስበዋል
የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የደረሰችውን ስምምነት ሊያከብሩ ይገባል ሲሉ የሶማሊያ መሪዎችን አስጠነቀቁ።
ፕሬዝዳንት ሙሴ ባሂ የኢትዮጵያ ጉባኝታቸውን አጠናቀው ሲመለሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አደባባይ ላይ ወጥተው ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ሙሴ ባሂ፤ ታሪካዊ ነው ባሉት የኢትዮጵያ ግብኝታቸው ከኢትዮጵያ እውቅና ሊያስገኝላቸው ስለሚችለው ስምምነት እና ስለ ሌሎች ስኬቶቻው አንስተዋል።
- ኢትዮጵያ ወደብ እንድትከራይ እና በምላሹ ለሶማሊላንድ እውቅና እንድትሰጥ ስምምነት ላይ መደረሱን ሶማሊላንድ አስታወቀች
- የኢትዮጵያን ቀይ ባህርን የመጠቀም ፍላጎት ያሳካል የተባለ የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን መንግስት ገለጸ
“ፕሬዝዳንት ሙሴ ባሂ በንግግራቸውም፤ ስምምነቱ በሶማሊላንድ እና በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት የተከናወነ” መሆኑን አስታውቀዋል።
“ከኢትዮጵያ ጋር የተደረሰው ስምምነት በሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት በሚፈቅደው አግባብ” እንደሆነ ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።
“በመግባያ ስምምነቱ መሰረት ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና የምትሰጥ መሆኑን እና በመትኩም በዓለም አቀፍ ህጎች መሰረት የወደብ መሬት በኪራይ እንደምታገኝ” ነው ፕሬዝዳነቱ የገለጹት።
“ሶማሊላንድ መሬቷን ለኢትዮጵያ ሸጠች የሚባለው ፈጽሞ ሀሰት ነው” ያሉት ፐሬዝዳነቱ፤ “የሶማሊላንድ መሬት አይሸጥም፤ ይህ የጠላት ወሬ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ሙሴ ባሂ በንግግራቸውም የሶማሊያ መሪዎች የማስጠንቀቂያ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ “የሶማሊላንድን የስኬቶችን ከማስቶጓጎል እንዲቆጠቡ” አሳስበዋል።
“የሶማሊያ መሪዎች ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ እውቅና ለማግኘት በደረሰችው የመግባቢያ ስምምነት ላይ ቅሬታቸውን እንዲያነሱም” አሳስበዋል።
“የሶማልላንድ ህዝብ ለሀገራቸው ጠቃሚ የሆነው ስምምነት ተግባራዊ እንዲደረግ ከሀገራቸው ጎን እንዲቆሙ” ፕሬዝዳነቱ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን የመጠቀም ፍላጎቷን ለማሳካት መንገድ የሚጠርግ እና የወደብ አማራጮችን የሚያሰፋ የመግባቢያ ሰነድ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ላይ ባሳለፍነው ሰኞ መፈራረሟ ይታወቃል።
ስምምነቱን የተቃወመው የሶማሊያ መንግስት በኢትዮጵያ የሚገኙትን የሀገሪቱን አምባሳደር አብዱላሂ መሀመድ ወርፋን ለምክክር ወደ ሞቃዲሾ መጥራቱን ይታወሳል።
ሶማሊላንድ በ1991 ነጻነቷን ብታውጅም ሞቃዲሾ አሁንም ድረስ የግዛቴ አካል ናት ብላ ታምናለች።