የሱዳን ጦር ተወካይ ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጋር በድጋሚ ንግግር ለመጀመር ጂዳ መድረሳቸው ተገለጸ
በሱዳን፣ በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል የተጀመረው ጦርነት ሶስተኛ ወሩን አስቆጥሯል
ቀደም ሲል ተደርገው የነበሩ ንግግሮች የተቋረጡት ተፋላሚዎቹ ባደረጉት ተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ጥሰት ምክንያት ነበር
የሱዳን ጦር ተወካይ ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጋር በድጋሚ ንግግር ለመጀመር ሳኡዲ አረቢያ ጅዳ መግባታቸው ተገልጿል።
በሱዳን፣ በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል የተጀመረው ጦርነት ሶስተኛ ወሩን አስቆጥሯል።
በአሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ አማካኝነት ቀደም ሲል ተደርገው የነበሩ ንግግሮች የተቋረጡት ተፋላሚዎቹ ባደረጉት ተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ጥሰት ምክንያት ነበር።
ሳኡዲ አረቢያና አሜሪካ ንግግሩ በድጋሚ ስለመጀመሩ አለማረጋገጣቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ከዚህ በተጓዳኝ ባለፈው ሀሙስ በግብጽ የተጀመረው የማደራደር ሙከራ በሱዳን ጦርና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በኩል ተቀባይነት አግኝቷል።
በሱዳን ለስለጣን እየተሻሙ ያሉት የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦርነቱ ከተጀመረ ከሚያዚያ ጀምሮ በርካታ ተኩስ አቁም ቢያውጁም ተግባራዊ አላደረጉም።
በጦርነቱ እስካሁን ሶስት ሚሊዮን ሰዎች ከቀያቸው ሲፈናቀሉ 700ሺ የሚሆኑት ደግሞ ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰድደዋል።
ተፋላሚዎቹ አሁንም በተለይም በካርቱም እና ባህሪ ከተሞች ውጊያ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ጦርነቱ ወደ እርስበእስርስ ግጭት ለመሸጋገር ጫፍ ላይ ደርሷል ሲል ተመድ ማስጠንቀቁ ይታወሳል።