የሱዳን ተፋላሚዎች ለ24 ሰአት እንዲቆይ የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ተጣሰ
የሱዳን ተኩስ አቁም ተግባራዊ ሊሆን ትንሽ ሲቀረው የተፈጠረው ተኩስ እንዲጣስ አድርጎታል
ተኩስ አቁሙ የተደረሰው አሜሪካ ሰብአዊ ቀውስ እንዳይፈጠር በማል በሱዳን ተፋላሚ ወገኞች ላይ ጫና ማሳደሯን ተከትሎ ነበር
የሱዳን ተኩስ አቁም ተግባራዊ ሊሆን ትንሽ ሲቀረው የተፈጠረው ተኩስ እንዲጣስ አድርጎታል።
ተኩስ አቁሙ የተደረሰው አሜሪካ ሰብአዊ ቀውስ እንዳይፈጠር በማል በሱዳን ተፋላሚ ወገኞች ላይ ጫና ማሳደሯን ተከትሎ ነበር።
ስምምነት ከተደረሰ ከደቂቃዎች በኋላ በካርቱም ዋና ከተማ የአረብ የቴሌቭዥን የዜና ማሰራጫዎች በቀጥታ ስርጭት ሲዘግቡ ከባድ ፍንዳታ ከጀርባ ይሰማ ነበር ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የጦር አውሮፕላኖች ከካርቱም በላይ ሰማይ ላይ እያገሱ እንደነበር እና በምስራቅ ወደ ከተማዋ ከፍተኛ የጦር ሰራዊት መግባቱን እማኞች ገልጸዋል።
የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ “ጦርነቱ መቆሙን የሚጠቁም ምንም ምልክት አልደረሰንም።"
በሱዳን ወታደራዊ መሪ እና ምክትላቸው መካከል የተፈጠረው ግጭት ከአራት ቀናት በፊት የተቀሰቀሰ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ የተደገፈውን ወደ ሲቪል ዲሞክራሲያዊ አገዛዝ ለመሸጋገር የተያዘውን እቅድ አደናቅፎታል።
ኢስላማዊው ገዢ ኦማር አልበሽር በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን ከወደቁ ከአራት አመታት በሱዳን ቀጣይነት አለመረጋጋት ውስጥ ነች።
ጦርነቱ የሱዳንን የጤና ስርዓት ውድቀት አፋጥኗል ብሏል።
በጦርነቱ እስካሁን ቢያንስ 185 ሰዎች መገደላቸውን ተመድ ገልጿልደ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ማክሰኞ ለሁለቱም የጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን እና ተቀናቃኛቸው መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ተቀናቃኛቸው ሃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ መጠየቃቸውን ተናግረዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የ24 ሰአት ተኩስ አቁም ያደረጉት ሱዳናውያን የሰብአዊ እርዳታ እንዲያገኙ ለማስቻል ነው።
በሱዳን የተቀሰቀሰው ግጭት ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል።