የአሜሪካ መንግስት ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወደ ዋድ መዳኒ የሚያደርጉትን የማጥቃት እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ በትናንትናው እለት ጥሪ አቅርባለች
የሱዳኑ ጀነራል ሄሜቲ ጦር ዋድ መዳኒ የተባለችውን ከተማ ለመያዝ ጦርነት ከፈተ።
በጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ ወይም ሄሜቲ የሚመሩት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ስምንት ወራትን ባስቆጠረው ጦርነት አዲስ ግንባር በመክፈት ዋድ መዳኒ የተባለችውን ከተማ ለመያዝ ከሱዳን ጦር ጋር እየተዋጉ ይገኛሉ።
በዋና ከተማዋ ካርቱም የተካሄደውን ግጭት ሸሸተው በዚህች ከተማ ተጠልለው የነበሩ ዜጎች ጓዛቸውን ጠቅልለው በእግራቸው ወደ ሌላ ቦታ እየሄዱ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሱዳን ጦር፣ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ በቁጥጥሩ ስር አድርጓት የነበረችውን የአል-ገዚራ ግዛት ዋና ከተማ ዋድ መዳኒን ላለማስነካት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን በከተማ ምስራቅ በኩል በአየር እየደበደ ይገኛል።
ባለፈው አርብ እለት በተጀመረው በዚህ ውጊያ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በከባድ መሳሪያ አጸፋ እየመለሰ እንደሆነ እና ተጨማሪ ኃይል ወደ ቦታው እያጓጓዘ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
ተመድ 14ሺ የሚሆኑ ሰዎች ቦታውን ለቀው ሸሽተዋል ብሏል። በአብዛኛው ከካርቱም የተሰደዱ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ስደተኞች ከለላ በመፈለግ ላይ ናቸው።
የሱዳን ዶክተሮች ህብረት በቦታው እንደሰብአዊ አገልግሎት እና የመድሂኒት መስጫ ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ሆስፒታል ቦዶ መሆኑን እና ሊዘጋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
ህብረቱ እንደገለጸው ከካርቱም ከሚገኘው ማይጎማ የወላጅ አልባ ማዕከል የመጡ 340 ህጻናት እና ሰራተኞች አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
የአሜሪካ መንግስት ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወደ ዋድ መዳኒ የሚያደርጉትን የማጥቃት እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ በትናንትናው እለት ጥሪ አቅርባለች።
አሜሪካ ይህን ያለችው በጥቃቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን በሚል ምክንያት ነው።
የሱዳኑን ግጭት በንግግር መፍትሄ ሰጥቶ ለማስቆም የተደረጉ ሙከራዎች አልተሳኩም።