ሱዳን፡ በግድቡ ድርድር ኢትዮጵያ “አራቱ አደራዳሪዎች ይግቡ” የሚለውን ሀሳብ እንድትቀበል በድጋሚ ጥሪ አቀረበች
አለመግባባቱን ተከትሎ ካርቱም “ወደ ሁለተኛ አማራጭ እየተሸጋገገረች” መሆኗ መገለጹ ይታወሳል
ያሲር አባስ፡ ኢትዮጵያ “የአራቱም አደራዳሪዎች ይግቡ” ሀሳብ አለመቀበሏ አስገርሞኛል ብለዋል
የሱዳን የመስኖ እና ውሀ ሀብት ሚኒሰትር ያሲር አባስ አለም አቀፉን የውሀ ቀን በካርቱም ሲከበር እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሁለቱም ሀገራት ማለትም ሱዳንና ግብፅን ልያስማማ የሚችለውን ወደ ትክክለኛውና ህጋዊ ስምምነትን ለመድረስ የሚያስችለውን “የአራቱም አደራዲሪዎች ይግቡ” ምክረ ሀሳብ እንድትቀበል ዳግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሚኒሰትሩ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት በተጨማሪ የተ.መ.ድ፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት አደራዳሪነት አለመቀበሏ እንዳስገረማቸውም ገልጸዋል፡፡ ሀገራቸው ሱዳን ባለፈው አመት የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ሚና ከፍ ሊል ይገባል የሚል ሀሳብ ስታቀርብ ኢትዮጵያ በፅኑ ስትቃውም እንደነበር በማስታወስ ጭምር፡፡
እናም ለሶስቱ ሀገራት ጥቅም ሲባል ኢትዮጵያ የአራቱም አደራዳሪዎች ይግቡ ሀሳብ ልትቀበል ይገባል ብለዋል የሱዳን የመስኖ እና የውሀ ሀብት ሚኒስትሩ ያሲር አባስ፡፡
የሶስቱም ሀገራት ድርድር ፡ኢትዮጵያ በቀጣይ ክረምት የሁለተኛው ዙር የግድቡ ሙሌትን አከናውናለው ማለትዋን እንዲሁም ግብፅና ሱዳን በተቃራኒ፤ ሙሌቱን እኛ ሳናምንበት የሚታሰብ አይደለም የሚሉ የሀሳብ ልዩነቶች ማንፀባረቃቸው ተከትሎ ለሳምንታት ቆሟል፡፡
ኢትዮጵያ ተመድ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ አሜሪካና የአፍሪካ ሕብረት በአደራዳሪነት ይግቡ የሚለውን ሀሳብ ውድቅ ማድረግዋን እንዲሁም የውሀ ሙሌቱ በተያዘለት መርሀ ግብር ይከናወናል የሚል ጠንካራ አቋም ማንፀባረቋን ተከትሎ ካርቱም “ወደ ሁለተኛ አማራጭ እየተሸጋገገረች” መሆኗ መገለጹ ይታወሳል፡፡ ይኸውም የውሃ እጥረት እንዳያጋጥማት በተለያዩ አማራጮች ውሃ ቀድሞ መያዝን የሚመለከት ነው፡፡