በሱዳን እስር ቤት በመሰበሩ የቀድሞው ኘሬዝደንት አልበሽር እጣ ፋንታ አልታወቀም
የደጋሎ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል የሱዳን ጦር እስረኞችን አስገድዶ ከእስርቤት እንዲወጡ አድርጓል ሲል ይከሳል
የሱዳን ጦር በበኩሉ ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ የእስር ቤት ፖሊሶችን በማስገደድ እስረኞች እንዲወጡ አድርጓል ሲል የቀረበበትን ክስ አይቀበልም
የቀድሞ ፕሬዝደንት አል በሽር የታሰሩበት እስርቤት ተሰብሯል፤ የኘሬዝደንቱ እጣ ፋንታ አልታወቀም።
ከሱዳን ኮበር አስረኞች ማምለጣቸውን ተከትሎ የቀድሞ ኘሬዝደንት አል በሽር ጉዳይ አወዛጋቢ ሆኗል።
የቀድሞ የሱዳን ፕሬዝደንት አልበሽር ታስረውበት የነበረው ኮበር እስር ቤት ተሰብሮ እስረኞች መውጣታቸውን ተከትሎ የፕሬዝደንቱ ጉዳይ አወዛጋቢ ሆኗል።
እስር ቤቱ የተሰበረው በሱዳን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ በሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል መካከል ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ነው።
አንድ የሱዳን ሚዲያ እንደዘገበው በሰሜን ካርቱም በሚገኘው የኮበር እስርቤት ዙሪያ ግጭት መከቱን እና በርካታ እስረኞች መለቀቃቸውን ዘግቧል።
አንድ በትዊተር የተሰራጨ ቪዲዮ ነጭ ዩኒፎርም የለበሱ አስረኞች በኮበር እስር ቤት ዙሪያ ወደላው መንገድ ሲወጡ ታይተዋል።
አል ዐይን ኒውስ የቪዲዮውን እውነት መሆኑን ማረጋገጥ አልቻለም።
የቀድሞ ፕሬዝደንት አልበሽርን ጨምሮ በርካታ አመራሮች በሚገኙበት የኮበር እስር ቤት ዙሪያ ግጭት ሲፈጠር አል ቡርሃን እና ደጋሎ ከተጋጩ ወዲህ ይህ የመጀመሪያ አይደለም።
ነገርግን በዛሬው እለት በእስር ቤቱ ዙሪያ የተካሄደው ግጭት ብዙ እስረኞች እንዲወጡና በሱዳን የተፈጠረው ግጭት እንዲባባስ አስተዋጽእ አድርጓል።
በርካታ እስረኖች መውጣታቸው በተለያዩ ቪዲዮዎች ቢሰራጩም፣ የአል በሽር እጣ ፈንታ ግን እስካሁን አልታወቀም።
አል በሽር ተለቋል፤ አልተለቀቀም የሚሉ እርስበእርስ የሚጋጩ ሪፖርቶች እየወጡ ነው።
የደጋሎ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል የሱዳን ጦር እስረኞችን አስገድዶ ከእስርቤት እንዲወጡ አድርጓል ሲል ይከሳል።
የሱዳን ጦር በበኩሉ ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ የእስር ቤት ፖሊሶችን በማስገደድ እስረኞች እንዲወጡ አድርጓል ሲል የቀረበበትን ክስ አይቀበልም።
የሱዳን ጦር፣ የደጋሎ ሀይል ከእስር ቤት በተጨማሪ የሱዳንን ስትራቴጂክ የአገልግሎት ተቋማትን ማጥቃቱን ገልጿል።