የሱዳን ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኘው ካምፓቸው ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ
የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲም ደህንነት ስላልተሰማቸው 1000 ስደተኞች ረቡዕ እለት ከኩመር ለቀው መውጣታቸው መረጃው አለኝ ብሏል።
በሱዳን የተቀሰቀሰውን ጦርነት ሸሽተው በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኘ የተመድ የስደተኞች ካምፕ ተጠልለው የነበሩ ስደተኞች ካምፓቸውን ለቀው መበተናቸው ተገልጿል
የሱዳን ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኘው ካምፓቸው ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ።
በሱዳን የተቀሰቀሰውን ጦርነት ሸሽተው በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኘ የተመድ የስደተኞች ካምፕ ተጠልለው የነበሩ ስደተኞች ካምፓቸውን ለቀው መበተናቸው ተገልጿል።
ሮይተርስ ስተደኞችን አናግሮ እንደዘገበው ቁጥራቸው ከ7000-8000 የሚደርሱ ስደተኞች በደረሰባቸው ጥቃት ምክንያት ባለፈው ረቡዕ እለት ኩመር የተባለውን ካምባቸውን ለቀው በእግራቸው ሄደዋል።
ከሱዳን 70 ኪሎሜትር ርቅት ላይ በኢትዮጵያ በአማራ ክልል ከሚገኘው ካምፕ ከወጡ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ በፖሊስ መያዛቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲም ደህንነት ስላልተሰማቸው 1000 ስደተኞች ረቡዕ እለት ከኩመር ለቀው መውጣታቸው መረጃው አለኝ ብሏል።
ሮይተርስ በዚህ ጉዳይ የኢትየጵያ መንግስት እና የአማራ ክልል ባለስልጣናትን ለማናገር ያደገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ገልጿል።
ባለፈው አመት ሚያዝያ በሱዳን ጦር እና በተቀናቃኙ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ከ1.6 በላይ የሚሆኑ ሱዳናውያን ከሀገራቸው ተሰደዋል።
በኩመር የሚኖሩት ስደተኞቹ እገታ፣ ግድያ እና ዘረፋ እንደሚፈጽምባቸው ለተመድ የሰብአዊ መብት ቢሮ በቅርቡ በጻፉት ደብዳቤ ማሳወቃቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በፌደራል መንግስት መካከል ባለፈው አመት የተጀመረው ግጭት አሁንም አልቆመም።
ሮይተርስ ያናገራቸው ስደተኞች እና ኤጀንሲው፣ ስደተኞቹ ካምፓቸውን ለመልቀቅ የተገደዱት ደህንነት ስላማይሰማቸው ነው ብለዋል።
ሳኡዲ አረባያ እና አሜሪካ በሱዳን የተጀመረው ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ አግኝቶ እንዲቋጭ በሳኡዲ አረቢያ ጅዳ አገናኝተው ለማደራደር ቢሞክሩም፣ እስካሁን አልተሳካም።