ሱዳን በኢትዮጵያ የሚገኙትን አምባሳደሯን በድንበሩ ጉዳይ ለማማከር ጠራች
የሁለቱ ሀገራት የድንበር ኮሚቴዎች ሁለት ጊዜ ከተሰበሰቡ በኃላ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም
በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረት የነገሰው የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ሲያርሱት የነበረውን መሬት ሱዳን ከሩብ ክፍለዘምን በኋላ “አስመልሻለሁ” ማለቷን ተከትሎ ነው
የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር የሆኑትን ጀማል አልሸህን በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር መካከል ስላለው የድንበር ችግር ለማማከር መጥሯቷን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ምንጮች ለአል ዐይን ኒውስ እንደገለጹት ሚኒስቴሩ አምባሳደሩን የጠራው ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የድንበር ቀውስ አንደምታ ለማማከር ነው፡፡ በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረት የነገሰው የሰዱን ጦር ወደ ምስራቃዊ ድንበር ወታደር መላኩን ካስታወቀና ሰፊ የሆነ የእርሻ መሬትን ከሩብ ክፍለዘምን በኋላ “አስመልሻለሁ” ማለቱን ተከትሎ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ይህን የሱዳንን እርምጃ በፍጹም አትቀበልም፤የሱዳን ጦርን ድንበሯን በመጣስ አርሶአደሮችን በማጥቃት ትከሳለች፡፡ ኢትዮጵያ አሁንም ሱዳን ከያዘችው ቦታ ለቃ እንድትወጣና ድንበር የማካለል ድርድሩ እንዲጀመር በተደጋጋሚ ጠይቃለች፡፡
የሁለቱ ሀገራት የድንበር ኮሚቴዎች ሁለት ጊዜ ከተሰበሰቡ በኃላ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ለ”ህግ ማስከበር ዘመቻ” በተሰማራበት ወቀት ሱዳን ክፍተቱን በመጠቀም የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ እንደገባች ኢትዮጵያ እየገለጸች ትገኛለች፡፡