የሱዳን መንግስት የኳታሩን አልጀዚራ ሙባሸር በሀገሪቱ የሚያከናውናቸውን ስራዎች እንዲያቆም አዘዘ
አልጀዚራ ሙባሸር የሱዳን ብሄራዊ ደህንነት የሚጎዱና ተገቢ ያልሆኑ ቪዲዮዎችን ያሲያስተላለፍ ነበር ተብሏል
ሚዲያው ሙያ ስነ ምግባር ከሚጠይቀው ውጭ ሲንቀሳቀስ ነበር በሚል ነው ውሳኔው የተላለፈበት
የሱዳን መንግስት የኳታሩን አልጀዚራ ሙባሸር በሀገሪቱ የሚያከናውናቸውን ስራዎች እንዲያቆም ትእዛዝ ማስተላለፉ ተገለፀ።
በዚህም መሰረት የሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስቴር ምክትል ፀሃፊ ዶ/ር ናስር ኤል-ዲን አህመድ መሀመድ ካሊድ በካርቱም ለሚገኘው የአልጀዚራ ሙባሸር ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር በፃፉት ኦደብዳቤ ሚድያው በሱዳን የሚያካናውናቸው ስራዎች እንዲያቆም ትእዛዝ አስተላልፈዋል።
የሱዳን ባለስልጣናት ከውሳኔው የደረሱት ሚዲያው ሙያዊ ስነ ምግባር ከሚጠይቀው ውጭ ሲንቀሳቀስ ነበር በሚል እንደሆነም ነው በተጻፈው ደብዳቤ የተመላከተው።
“አልጀዚራ ሙባሸር፤ በሱዳን ጉዳይ ሙያዊ ስነምግባር በጎደለው መልኩ እንዲሁም የሱዳን ሕዝብ ሥነ ጽሑፍ የሚጻረር ይዘትን በመገናኛ ብዙኃን በማስተላለፍ የሀገሪቱን ማህበራዊ ገጽታ በማጠልሸት ላይ ነበር” ነው የሚለው የደብዳቤው ይዘት።
የኳታሩ ቻናል የሀገሪቱን ከፍተኛ ጥቅምና ብሄራዊ ደህንነት የሚጎዱ "አፀያፊ ቃላት፣ ተገቢ ያልሆኑ ቪዲዮዎች እና ያረጁ ትዕይንቶች" ሲያስተላለፍ ነበረም ነው የተባለው።
ከኳታሩ አልጀዚሪያ ሚዲያ ኔትዎርክ ውስጥ አንዱ የሆነው አልጀዚራ ሙባሸር፤ በፈረንጆቹ ሚያዚያ 15 2005 ነው በይፋ ተመስርቶ ስራ የጀመረው።
በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ቴሌቪዥን ጣቢያው ኮንፍረንሶችን እና ሌሎች ሁነቶችን ያለ ምንም ማብራሪያ በቀጥታ እንደወረደ የሚያስተላለፍ ሲሆን፤ እንደ አስፈላጊነቱ የፅሁፍ መሸጋገሪያ ሊገባ ይችላል።