ኢኮኖሚ
ስዊዝ ባንክ በካዝናው ምን ያህል የሩሲያ ሀብት እንዳለ ይፋ አደረገ
ስዊዝ ባንክ ገንዘብን በአስተማማኝ መልኩ ለማስቀመጥ የሚመረጥ ስመጥር ባንክ መሆኑ ይነገራል
ባንኩ የፕሬዝዳንት ፑቲንና የ370 ፖለቲከኞችና የቢዝነስ ባለቤቶችን ሀብት እንዳይንቀሳቀስ ሊያግድ ነው
ስዊዝ ባንክ የሩሲያ ደንበኞቹ ምን ያህል ተቀማጭ ገንዘብ እንዳላቸው ይፋ ማድረጉን የሩሲያው ቴሌቪዥን አርቲ አስታወቀ።
የስዊዝ ባንኮች ማህበር ሩሲያውያን በባንኩ ያስቀመጡትን ገንዘብ ይፋ ማድረጉን ገልጿል። በዚህም መሰረት የሩሲያ ደንበኞቹ በባንኩ ከ 160 እስከ 213 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ እንዳስቀመጡ ነው ባንኩ የተናገረው።
ስዊዝ ባንክ ገንዘብን በአስተማማኝ መልኩ ለማስቀመጥ የሚመረጥ ስመጥር ባንክ መሆኑ በተደጋጋሚ ይነገራል።
ይሁንና ባንኩ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚርን እና የ 370 ፖለቲከኞችና የቢዝነስ ባለቤቶችን ሀብት እንዳይንቀሳቀስ ሊያግድ ነው ተብሏል።
ስዊዝ ባንክ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው የአውሮፓ ሕብረት በሩሲያ ባለሀብቶች ላይ እገዳ ከጣለ በኋላ ነው ተብሏል።
ሩሲያውያን ባለሀብቶች በተናጠል በአጠቃላይ ደግሞ ሀገሪቱ ፤ በአውሮፓና በአሜሪካ ተደጋጋሚ እገዳዎች እያጋጠሟቸው ቢሆንም ሞስኮ ግን “አልበገረም” እያለች ነው።