ከተማሪዋ ያረገዘችው መምህር በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባለች
መምህሯ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ከሆኑ ታዳጊዎች ጋር ወሲብ በመፈጸም ተከሳለች
ከሁለት ታዳጊዎች ጋር ወሲብ ፈጽማለች የተባለችው መምህር ከወራት በፊት ልጅ መውለዷ ተገልጿል
ከተማሪዋ ያረገዘችው መምህር በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባለች
ርብቃ ጆይንስ የተባለችው የ28 ዓመት መምህር በማንችስተር ከተማ ባለ ትምህርት ቤት ውስጥ መምህር ነበረች፡፡
ይህች መምህር ከምታስተምራቸው ታደጊዎች ጋር ወሲብ ፈጽማለች የተባለ ከታዳጊዎቹ ትኩረት ማግኘቷ ግንኙነቱን እንድትመሰርት እንዳነሳሳት ተናግራለች፡፡
የ15 ዓመት እድሜ አላቸው የተባሉት እነዚህ ሁለት ታዳጊዎች በተለያዩ ጊዜያት ከመምህራቸው ጋር ወሲብ እንደፈጸሙ ሁኔታው በወላጆቻቸው ከታወቀ በኋላ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ማምራቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ለ20 አመታት በስራ ገበታቸው ያልተገኙት ጣሊያናዊት መምህርት በመጨረሻም ተባረዋል
መምህሯ በፍርድ ቤት ቀርባ እንደተናገረችው ድርጊቱን እንደፈጸመችው አምና ቃሏን ሰጥታለች፡፡
ተከሳሿ ለሰባት ዓመታት ከነበረችበት የፍቅር ግንኙነት መለያየቷ ያደረሰባት የስነ ልቦና ጉዳት ከታዳጊዎቹ ያገኘችው ትኩረት ወንጀሉን እንድትፈጸም እንዳነሳሳት በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ማህበራዊ የትስስር ገጾች ከታዳጊዎቹ ጋር ለመደዋወል ረድቷታል የተባለ ሲሆን መጀመሪያ ላይ ስናፕ ቻት በተሰኘው የትስር ገጽ ላይ መልዕክት እንደተላላኩም ተገልጿል፡፡
ከጥቂት ወራት በፊት ልጅ ወልዳለች የተባለ ሲሆን የመምህሯ ወላጆች ከልጃቸው ጋር አብረው ፍርድ ቤት እንደተገኙም ተጠቅሷል፡፡
መምህሯ ለአካላ መጠን ካልደረሱ ታዳጊዎች ጋር ወሲብ በመፈጸም ጥፋተኛ የተባለችው ይህች መምህርት በፈረንጆቹ ሀምሌ አራት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡