በአለማቀፉ የሽብርተኝነት ሪፖርት ቡርኪናፋሶ በሽብር ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች
ባለፈው የፈረንጆቹ አመት በተለያዩ የአለም ሀገራት የተመዘገበው የሽብር ጥቃት ከ2017 ወዲህ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
በ2023 ከ3 ሺህ 500 በላይ የሽብር ጥቃቶች ደርሰው የ 8 ሺህ 352 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአለማቀፉ የሽብርተኝነት ሪፖርት አመላክቷል።
በአለማቀፉ የኢኮኖሚና ሰላም ተቋም የተደረገው ጥናት ከ13 አመት በኋላ አፍጋኒስታን እና ኢራቅ ከቀዳሚዎቹ የሽብር ተጠቂ ሀገራት ዝርዝር የወጡበት አልያም ደረጃቸው ዝቅ ያለበት መሆኑን አሳይቷል።
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ ከ258 በላይ የሽብር ጥቃቶች ተፈጽመውባት 2 ሺህ የሚጠጉ ዜጎቿ ህይወት አልፏል።
ኢራቅ ለመጀመሪያ ጊዜ በሽብር ጥቃት ከባድ ጉዳት ካስተናገዱ 10 ሀገራት ዝርዝር ውስጥ በወጣችበት አመት፥ አፍጋኒስታን ደረጃዋ ወደ ስድስተኛ ዝቅ ብሏል።
በተፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች ብዛት ፓኪስታን ቀዳሚ ስትሆን፥ 490 ጥቃቶች ደርሰውባታል።
በሽብር ጥቃቶች ከተመዘገበው ሞት የሰሃራ በታች የአፍሪካ ሀገራት፣ የመካከለኛው ምስራቅ እና የደቡብ እስያ ሀገራት ድርሻ 94 በመቶ ነው ተብሏል።
እስራኤል እና ማሊን ከቡርኪናፋሶ ቀጥሎ ያስቀመጠው የአለማቀፉ የሽብርተኝነት ኢንዴክስ፥ ባለፈው አመት የተመዘገበው የሽብር ጥቃት ብዛት ከ2022 በ22 በመቶ መቀነሱን አመላክቷል።
ሪፖርቱ ባለፈው የፈረንጆቹ አመት ከሽብር ጥቃት ጋር በተገናኘ በ41 ሀገራት ሞት መመዝገቡንም ነው ያሳየው።
በ2023 በሽብርተኝነት ከባድ ዋጋ የከፈሉ 10 ሀገራትን ይመልከቱ፦