የ2012 ሀገር አቀፍ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን ነሀሴ 23 ሆኗል
የ2012 ሀገር አቀፍ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን ነሀሴ 23 ሆኗል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ በፊት ነሐሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ምርጫ ይደረጋል ብሎ የነበረ ቢሆንም ከብዙ ምክክር በኋላ ይህንን ዕለት አሻሽሎታል፡፡
የ2012 ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከልሶ በቀረበው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የድምፅ መስጫ ቀን ነሀሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሆኗል።
ቦርዱ ይህንን ይፋ ያደረገው ዛሬ በአዲስ አበባ ከሚመለከታቸው የምርጫ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባደረገበት ጊዜ ነው፡፡
በባለድርሻ አካላት ኮንፈረንሱ የተሻሻለውን የምርጫ ሰሌዳ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አቅርበውታል።
ከዚህ ቀደም ጊዜያዊ የድምፅ መስጫ ቀን ነሀሴ 10 ቀን እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል።
የምርጫ ጊዜውን ለማራዘም የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ግንዛቤ ውስጥ ብናስገባም ከህግ አንፃር የተከለሰው የድምፅ መስጫ ቀን ነሀሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ይሆናል ብለዋል ሰብሳቢዋ።
በክረምት መካሄዱ ሊፈጥር የሚችለውን ተፅእኖ በተመለከተም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ብሔራዊ ሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ በጋር እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡