በብሉ ናይል ክልል ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ220 አልፏል
የሱዳን መንግስት በብሉ ናይል ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታወቀ።
በብሉ ናይል ክልል ግጭት የተቀሰቀሰው ባለፈው ሳምንት በሃውሳ ህዝቦች እና በተቀናቃኝ ቡድኖች መካከል በመሬት ጉዳይ ላይ አለመግባባት ከተስተዋለ በኋላ ግጭት ተቀስቅሷል።
ይህንን ተከትሎ በሁለት ቀን ግጭት ብቻ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 223 መድረሱን የዋድ አል ማሂ ሆስፒታል ኃለፊ አባስ ሙሳ አስታውቀዋል።
ከእነዚህም መካከል ሴቶች እና ህጻናት ይገኙበታል የጠባለ ሲሆን፤ ከሞቱት በተጨዋሪም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸውን ኃላፊው አክለው ገልጸዋል።
በተጨማሪም ግጭቱን ተከትሎ ከቤት ንረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ከ800 በላይ መድረሱን ብሉ ናይል ክልል አስታውቋል።
የብሉ ናይል ክልል አስተዳዳሪ እንዳስታወቁት ከሆን መሳሪያ ልታጠቁ ሰዎች ብሉ ናይል ክልልን ከካርቱም ጋር የሚያናኘውን ለመቁረጥ እየመከሩ መሆኑን እና ንጹሃንንን እየገደሉ መሆኑን ገልጸዋል።
ግጭቱ ወደሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ሊስፋፋ እንደሚችልም ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።
ይህንን ተከትሎም የሱዳን መንግስት ግጭቱን ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ በቡሉ ናይል ክልል የአስኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉ ታውቋል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሱዳን እየተስተዋለ የመጣው ጎሳ ግጭት ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ኪሳራ ከማስከተሉም ለዴሞክራሲያዊ ሽግግርና ለሰላም ሂደቱ አንዱ ጠንቅ እንደሆነ ይነገራል።
በርካቶችም የጎሳ ግጭት ሱዳን የምትታመምበት መቅሰፍት ነው ሲሉ ይደመጣሉ፡፡