ልዩልዩ
ሳዳም ሁሴን በስቅላት እንዲገደሉ የፈረዱት ዳኛ ህይወት አለፈ
የቀድሞው ኢራቅ ፕሬዝዳንት ሳዳም ሁሴን በጎርጎሮሳውያኑ 2006 በባግዳድ በስቅላት መገደላቸው የሚታወስ ነው
መሀመድ አሪቢ መጂድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ነው ህይወታቸው ያለፈው ተብሏል
በቀድሞው የኢራቅ ፕሬዝዳንት ሳዳም ሁሴን ላይ የሞት ፍርድ ያስተላለፉት ዳኛ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አለፈ።
የኢራቅ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ዳኛ መሀመድ አሪቢ መጂድ በኮሮና ቫይረስ ምከንያት ህይወታቸው አልፏል።
የቀድሞው ኢራቅ ፕሬዝዳንት ሳዳም ሁሴን የኒውክሌር ጦር አላቸው በሚል በአሜሪካ እና እንግሊዝ ጥምር ጦር አማካኝነት በተደረገ ዘመቻ መንግስታቸው መፍረሱ ይታወሳል።
በመጨረሻም ሳዳም ሁሴን ታህሳስ 1998 ዓ/ም ከተደበቁበት ዋሻ ተይዘው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሞት ፍርድ ተላልፎባቸው በባግዳድ በስቅላት መገደላቸው አይዘነጋም።
ሳዳም ሁሴን በተከሰሱበት የዘር ማጥፋት ወንጀል እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥፋተኛ ናቸው በሚል የሞት ፍርድ ያስተላለፉት ዳኛ መሀመድ አሪቢ በተወለዱ በ52 ዓመታቸው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።