አባ ፍራንቼስኮስ የኢራቅ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ቫቲካን ተመለሱ
በከፋ የጸጥታ ችግር ውስጥ ትገኛለች ወደሚባልላት ኢራቅ ያቀኑ የመጀመሪያው ጳጳስም ናቸው
አባ ፍራንቸስኮስ ያሳለፍነው አርብ ነበር በኢራቅ የሚገኙ ክርስቲያኖችን ለማጽናናት ያላቸውን አጋርነትም ለማሳየት በሚል ወደ ባግዳድ ያቀኑት
ለ4 ቀናት “ሐዋርያዊ ጉብኝት” ወደ ኢራቅ አቅንተው የነበሩት የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ቫቲካን ተመለሱ፡፡
አባ ፍራንቸስኮስ ያሳለፍነው አርብ ነበር በኢራቅ የሚገኙ ክርስቲያኖችን ለማጽናናት ያላቸውን አጋርነትም ለማሳየት በሚል ወደ ባግዳድ ያቀኑት፡፡
በነበራቸው ቆይታም ከሃገሪቱ የተለያዩ ባለስልጣናት እና የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ከምዕመናን ጋር መክረዋል፡፡
በጽንፈኛው አይ ኤስ እና በሌሎችም ጦርነቶች ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸውን ሞሱል እና ኤርቢልን እንዲሁም ቃራኮሽን ጨምሮ ሌሎችንም ከተሞች ጎብኝተዋል፡፡
ቆይታቸውንም አጠናቀው ዛሬ ጠዋት ወደ ጣሊያን ሮም ቫቲካን ተመልሰዋል፡፡
ሴቶችን በሙሉ በተለይም ደግሞ “በስህተቶች እና ጉዳቶች መካከል ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል” ያሏቸውን የኢራቅን ሴቶች ያመሰገኑት ፍራንቸስኮስ በአክብሮት ሊታዩ እና ሊጠበቁ እንደሚገባም አሳስበዋል በስማቸው ባለው ይፋዊ የማህበረሰብ ትስስር ገጽ ባሰፈሩት ጽሁፍ፡፡
የዓለም ካቶሊካውያኑ አባት በከፋ የጸጥታ ችግር ውስጥ ትገኛለች ወደሚባልላት ኢራቅ ያቀኑ የመጀመሪያው ጳጳስ ናቸው፡፡