መጽሔቱ በአፍሪካ ቀንድ ታሪክ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን በአካባቢው ሲሰነዘሩ የነበሩ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ያስተካክላል ተብሏል
መጽሔቱ በአፍሪካ ቀንድ ታሪክ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን በአካባቢው ሲሰነዘሩ የነበሩ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ያስተካክላል ተብሏል
በአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦች ታሪክና ባህል ላይ ትኩረቱን ያደረገ እና በአረብኛ ቋንቋ የተዘጋጀ የመጀመሪያው መጽሄቱ “አል ቀርን አልአፍሪቂ” ይሰኛሉ፡፡መጽሔት ለህትመት መብቃቱን የአፍሪካ ቀንድ የታሪክ ጥናት ማዕከል አስታወቀ፡፡
የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አማን ጉደታ እንደገለጹት መጽሔቱ በአፍሪካ ቀንድ ታሪክ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን በአካባቢው ሲሰነዘሩ የነበሩ የተሳሳቱ አመለካከቶችን እንደሚያስተካክል ተናግረዋል፡፡
መጽሔቱ በኢትዮጵያ በአረብኛ ቋንቋ የመጀመሪያው የባህል ታሪካዊ መጽሔት ሲሆን በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ምሁራንና ተመራማሪዎችና ተሳትፈዋል ተብሏል ፡፡
ስለቀጣናው የነበረውን የሀሰት ትርክትን ለማስተካልና እና የሕዝቦችን ታሪክ በማጥናትና ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ አቅም እንደሚሆንም ነው ዋና ሥራ አስኪያጁ የተናገሩት፡፡ ማዕከሉ የታሪክ መጻሕፍትንና መጽሔቶችን በማዘጋጀት እንዲሁም ታሪካዊ መጻሕፍትን ከውጭ ቋንቋዎች ወደ አካባቢያዊ ቋንቋዎች በመተርጎም እስካሁን ያልተነገሩትን እውነታዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነውም ብለዋል፡፡