የግድቡ ዋነኛ ስራ የሚከናወነው በዚህ አመት ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ግድቡ እንዲደናቀፍ የሚፈልጉ የውስጥም የውጭም ኃይሎች አሉ ብለዋል
የህዳሴው ግድብ በባለፈው አመት በተካሄደው የመጀመሪያ ሙሌት 4.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዙ ይታወሳል
የህዳሴው ግድብ በባለፈው አመት በተካሄደው የመጀመሪያ ሙሌት 4.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዙ ይታወሳል
ኢትጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባቸው ያለው ግድብ ዋነኛ ሥራ በዚህ ዓመት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድቡን አስመልክቶ ከምክር ቤት አባል ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ከባለፈው ዓመት በተለየ መልኩ ዘንድሮ የተለየ ስራ እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡ ይህንንም በሕዳሴ ፕሮጀክት ለሚሰሩ ሰራተኞች መንገራቸውን አስታውቀዋል፡፡
በዚህ በጀት ዓመት ሁለቱም ማለቱም የኤሌክትሮ መካኒካልና የሲቪል ስራው ከሌሎቹ ዓመታት በተለየ ፈታኝ እንደሚሆን እንደሚጠበቅ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ግን ብዙ እንቅፋቶች እንደሚኖሩም ገልጸዋል፡፡
ሕዳሴ ግድብ እንዲደናቀፍ የሚፈልጉ የውስጥም የውጭም ኃይሎች እንዳሉ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህ በራሱ ዕድልም ችግርም ነው ብለዋል፡፡ በአንድ በኩል እንዲደናቀፍ የሚፈልጉ ሰዎች መኖራቸው ትኩረት ሰጥተን እንድንመራው ያደርጋል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከሰነበቱት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን ከሰሞኑ በግንባታ ላይ ያለውን የሕዳሴ ግድብ ጎብንተዋል፡፡
ህዳሴ ካለፈው ይልቅ በገንዘብ፣ በቴክኒክ እና ምህንድስና ስራም አንጻር ወደፊት ብዙ ሥራን የሚጠይቅ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፕሮጀክቱ ዕድልም ተግዳሮትም አጣምሮ የያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ተቋርጦ የነበሩት የሀይድሮ፣ ሶላር፣ ጂኦተርማል ዘርፎች የሚገኙበት የኮይሻ ፕሮጀክት እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የግድቡን የመጀመሪያ ሙሌት በ2012ዓ.ም አከናውናለች፤ 4.9 ቢሊዮን ኪውቢክ ሜትር ውሃም ይዛል፡፡ ኢትዮጵያ ግድቡን ለሙላት እቅድ ባስቀመጠችበት ወቅት ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ተቃውሞ ገጥሟጽ ነበር፡፡ ነገርግን ኢትዮጵያ በእቅዷ መሰረት የመጀመሪያው አመት ሙሌት ማከናወኗ ይታወሳል፡፡