
በግድያ ሙከራው ላይ በነበረው ፍንዳታ የፕሬዚዳንቱ ጠባቂዎች መሞታቸው ታውቋል
የፑትላንት ፕሬዚዳንት ሰይድ አብዱላሂ ዴኒ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ መትረፋቸው ተገለፀ።
ግድያ ሙከራው በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ በምትገኘው ቦሰቦ ከተማ መፈፀሙን የፀጥታ አካላት አስታውቀዋል።
የአካባው መገናኛ ብዙሃን፤ ፕሬዚዳንቱ ወደ ከተመዋ የሚያስገባውን ዋናውን መንገድ ይዘው በመጓዝ ላይ እያሉ የሚጠቀሙበትን መኪና ኢላማ ያደረገ ፍንዳታ መከሰቱን አስታውቀዋል።
የጠፀጥታ ኃላፊዎች ለአል አይን ኒውስ እንደተናገሩት፤ ፍንዳታው የተከሰተው ወደ ከተመዋ በሚያሰስገባ የፍተሸ ጣቢያ ላይ በተጠመደ ቦምብ ነው።
ፕሬዚዳንት ዴኒ ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጥቃቱ ማምለጣቸውን ያስታወቁት የፀጥታ አካላቱ፤ የፕሬዚዳነቱ ጠባቂዎች ላይ ግን ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል።
በዚህም ሁለት የፕሬዚዳንቱ ጠባቂ ወታደሮች የሞቱ ሲሆን፤ ሌሎች አራት የጥበቃ ቡድኑ አባላት ደግሞ መቁሰላቸውን ገልፀዋል።
የፑንትላንድ ግዛት መሪ የሆኑት ፕሬዚዳንት ሰይድ አብዱላሂ ዴኒ በቦሳሶ ከተማ ጉብኝት በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል።
ፕሬዚዳንቱ በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ በምትገኘው ቦሰቦ ከተማ የሚያደርጉት ጉብኝት ከቀናት በኋላ በሶማሊያ የፌዴራል ፓርላማ 16 መቀመጫዎችን ለማግኘት የሚደረገውን የተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ሂደትን ለመገምገም እንደሆነም ተነግሯል።