በጋምቤላ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰም የክልሉ መንግስት አስታውቋል
ጋምቤላ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰ የክልሉ መንግስት አስታወቀ።
ርዕሰ መስተዳድር ኡመድ ኡጁሉ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ በነበረው ተኩስ በከተማው በሚገኙ የመንግስት ተቋማት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ከጥቂት ሰዓታት በፊት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ተኩስ የከፈቱት ቡድኖች የርዕሰ መስተዳድሩን ቢሮ እንደተቆጣጠሩ ተደርጎ የተናፈሰው ወሬ ሀሰት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል።
በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በክልሉ የሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ባካሄዱት "ቅንጅታዊ ማጥቃት" ከተማውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
ተከፍቶ በነበረው ተኩስ የጉዳቱ መጠን ቢለያይም ከሁሉም ወገን ጉዳት ደርሷልም ነው ያሉት።
ርዕሰ መስተዳድሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተኩስ ከፍተው በነበሩ ሃይሎች ላይ የፀጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ ከተማዉን ማረጋጋት ተችሏል ብለዋል።