ፑቲንን ለማግኘት ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን የሮማው ጳጳስ ፍራሴስ ተናገሩ
ጦርነቱ በተጀመረ በሶስት ሳምንታት ውስጥ ያቀረቡት ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱን ፍራንሴስ ተናግረዋል
ፑቲን መገናኘቱን ላይፈልጉት ይችላሉ በሚል መስጋታቸውን ፍራንሴስ ገልጸዋል
ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሞስኮ ተገናኝቶ ለመምከር ጥያቄ ማቅረባቸውን የሮማ ጳጳስ እና የዓለም ካቶሊካውያን አባት ተናገሩ፡፡
ከጣሊያኑ ኮሬ ዴላ ሴራ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ሞስኮው መምጣት እፈልጋለሁ ሲሉ ለፑቲን መልዕክት መላካቸውን ተናግረዋል፡፡
መልዕክቱ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት በተጀመረ በ20ኛው ቀን የተላከ መሆኑንም ነው ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ የተናገሩት፡፡
ሆኖም እስካሁን ለጥያቄው ምላሽ አላገኘንም ብለዋል፤ አሁንም እየሞከሩ መሆኑን በመጠቆም፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን መገናኘቱን ላይፈልጉት ይችላሉ በሚል መስጋታቸውንም ፍራንችስኮስ አልሸሸጉም፡፡
ከ25 ዓመታት በፊት በሩዋንዳ የነበረውን ጭፍጨፋ በማስታወስም እንዲህ ዐይነቱ አሰቃቂ ሁኔታ ለምን አይቆምም ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
በ1997ቱ የሩዋንዳ ጭፍጨፋ 800 ሺ ገደማ ቱትሲዎች መገደላቸው ይታወሳል፡፡
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት እንዲቆም ደጋግመው የጠየቁት ፍራንችስኮስ ከዩክሬን ይልቅ ወደ ሩሲያ መሄዱን እንደሚያስቀድሙ ተናግረዋል፡፡
ወደ ሞስኮው ለማቅናት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የሚያገኝ ከሆነ በሞስኮው ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ክሪል ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩም ነው የተናገሩት፡፡