በጀርመን የፓርላማ ምርጫ የተሰናባቿ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ፓርቲ ተሸነፈ
ያለፉትን 16 ዓመታት በመራሂተ መንግስትነት ያሳለፉትና ከፓርቲ ሊቀመንበርነታቸው ጡረታ የወጡት አንጌላ ሜርክል ምርጫውን ተከትሎ ስልጣን የሚለቁ ይሆናል
አብላጫ ድምጽ ያኙት ሶሻል ዴሞክራቶች 206 የቡንደስታግ መቀመጫዎችን ይዘዋል
በጀርመን የቡንደስታግ (ፓርላማ) ምርጫ የተሰናባቿ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ፓርቲ ተሸነፈ፡፡
ጥምሩ ዩኒዬን ፓርቲ (CDU / CSU) የተሸነፈው ዛሬ ከተሰጠው ድምጽ አብላጫውን ባገኙ ሶሻል ዴሞክራቶች (SPD) ነው፡፡
ተሰናባቿ የጀርመን አምባሳደር ስለ ኢትዮጵያ በተጨባጭ ያሉት ምንድነው?
የምርጫው የቅድመ ምርጫ ውጤቶች በኦላፍ ሾልዝ የሚመራው ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (SPD) እየመራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
735 መቀመጫዎች ካሉት የሃገሪቱ ፓርላማ (ቡንደስታግ) 206 ያህሉን ማሸነፉንም ነው ያመለከቱት፡፡
SPD እስካሁን ከተሰጡት ድምጾች 25 ነጥብ 7 በመቶ ያህሉን በማግኘት 196 የቡንደስታግ መቀመጫዎችን ማሸነፉን የሃገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡
ጀርመን በቅኝ ግዛት ዘመን የወሰደቻቸውን ቅርሶች ለናይጀሪያ ልትመልስ መሆኗን አስታወቀች
አንጌላ ሜርክልን ለመተካት አርሚን ላሼትን እጩ አድርጎ ያቀረበው ዩኒዬን ፓርቲ ደግሞ ባለፉት 16 ዓመታት አግኝቶት የማያውቅ ነው የተባለውን የድምጽ ውጤት አግኝቶ በ24 ነጥብ 1 በመቶ እየተከተለ ነው፡፡
ምርጫውን ተከትሎ የአንጌላ ሜርክል የ16 ዓመታት የመራሂተ መንግስትነት ጉዞ የሚያበቃ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ሜርክል ከዩኒዬን ፓርቲ ሊቀመንበርነታቸው መልቀቃቸውም የሚታወስ ነው፡፡