ፖለቲካ
ዩኤኢ ለሊቢያ ህዝብ እና መንግስት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች
የሊቢያ ፓርላማ ዛሬ በዲቤባ ለሚመራው የአንድነት መንግስት የመተማመኛ የድጋፍ ድምጽ መስጠቱ ይታወሳል
ሊቢያውያን መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማቸው የተመኘችው ዩኤኢ ድጋፏ እንደማይለያቸውም አስታውቃለች
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የአብዱል ሃሚድ አል ዲቤባ መንግስት የሃገሪቱን ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ የድጋፍ ድምጽ በማግኘቱ ለሊቢያ ህዝብ እና መንግስት የእንኳን ደስ አላችሁ መንግስት አስተላለፈች፡፡
ዩኤኢ የፕሬዝዳንቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙሃመድ ዩኑስ አል ማንፊን እና ምክትሎቻቸውን እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎች የካቢኔ አባላትን እንኳን ደስ አላችሁ ብላለች፡፡
ወንድም ላለችው ለሊቢያ ህዝብ ፍላጎት ስኬት በሚያደርጉት ጥረት መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማቸውም ተመኝታለች፡፡
ዩኤኢ ለዚህ ታሪካዊ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ ልዩ መልዕክተኛንና ሙሉ የድርጅቱን ተልዕኮ አባላትም ነው አድንቃ እንኳን ደስ አላችሁ ያለችው፡፡
ከአሁን በኋላም ቢሆን በድርጅቱ ክትትል ስር ለሚተገበረው ፍኖተ ካርታ ሙሉ ድጋፍ እንደማይለይ ነው ያረጋገጠችው፡፡