ተመድ የሱዳንን ፖለቲካዊ ቀውስ ለመፍታት የመጀመሪያውን የምክክር መድረክ ማጠናቀቁን አስታወቀ
በሱዳን የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የሀገሪቱ ጦር በወሰደው እርምጃ 79 ሰዎች ሞተዋል
የሱዳን የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን መንግስተ ማፍረሳቸውን ተከትሎ ሱዳን በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብታለች
በሱዳን የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ተልዕኮ በሀገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ቀውስ ለማስቆም ከሱዳን ፓርቲዎች ጋር ያደረገውን የመጀመሪያ ደረጃ ምክክር በትናንትው እለት ማጠናቀቁን አስታውቋል።
በሱዳን የሚገኘው የተመድ የተቀናጀ የሽግግር ዕርዳታ ተልዕኮ በሲቪል አስተዳደር ሽግግር ይደረግ በሚለው አወዛጋቢ ጉዳይ ላይ የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች የተስማሙባቸውን ጉዳዮች የያዘ ሰነድ ያዘጋጃል ተብላል፡፡
የተመድ የተቀናጀ የሽግግር ዕርዳታ ተልዕኮ ኃላፊ ቮልከር ፔርቴስ፣ ተልእኮው የተለያዩ አመለካከቶችን እና የውሳኔ ሃሳቦችን ከሱዳን ህዝብ ለመስማት የሚያስችል በመሆኑ የምክክር ሂደቱን ጠቃሚ ነው ሲሉ ገልጸውታል።
በፈረንጆቹ ጥር 10 የተመድ ልኡክ በሱዳን ያለውን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት በሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ንግግር ሂደት መጀመሩ ይታወሳል።
የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን በጥቅምት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጁ እና ሉዓላዊ ምክር ቤቱን እና መንግስትን ከፈረሰ በኋላ ሱዳን በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች።
በሉላዊ የሽግግር መንግስቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አብደላ ሀምዶክ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ሱዳን በማያባራ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብታለች።
የሱዳን ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ የሲቪል መንግስት አስተዳደር እንዋቀር የሚጠይቁ ሰልፎች ሲያካሂዱ ቆይተዋለክ፤እያካሄዱም ይገኛሉ።
የሱዳን ጦር ከዚህ በፊት በተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በወሰደው እርምጃ 79 ዜጎች መገደላቸውን የሱዳን ሀኪሞች ማህበር መግለጹም ይታወሳል።
ምንም እንኳ በሱዳን የሲቪል ወታደሩ ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስተላለፍ የሚጠይቁ ሰልፎች በቢረቱም፤ በጀነራል አልቡርሀን የሚመራው የሱዳን ጦር በበኩሉ በምርጫ ላልተመረጠ መንግስት ስልጣን እንደማይሰጥ መግለጹ ይታወሳል።