በኦነግ ውስጥ የአመራር ለውጥ እንዳልተደረገ ተገለጸ
የኦነግ ሊቀመንር ዳውድ ኢብሳ ቤት በመንግስት እየተጠበቀ መሆኑን ፓርቲው በትናንትናው እለት ገልጿል
የኦነግ ሊቀመንበር ስራቸውን ማከናወን ባለመቻላቸው በጊዜያዊነት መተካታቸውን የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት አስታወቁ
የኦነግ ሊቀመንበር ስራቸውን ማከናወን ባለመቻላቸው በጊዜያዊነት መተካታቸውን የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት አስታወቁ
በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ውስጥ የተደረገ የአመራር ለውጥ አለመኖሩን የግንባሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስታወቁ፡፡
በዛሬው እለት በኦነግ ውስጥ የአመራር ለውጥ እንደተካሄደ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የነበረው መረጃ ትክክል አለመሆኑን ግንበሩ አስታውቋል፡፡
ከአል ዐይን ጋር በሥልክ ቆይታ ያደረጉት አቶ ቀጀላ፣ የግንባሩ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ለጊዜው ሥራቸውን ማከናወን ስላልቻሉ እርሳቸውን ተክቶ ሌላ አመራር ሥራውን እያከናወኑ ነው ብለዋል፡፡ በዚህም መሰረት አቶ አራርሶ ቢቂላ ለጊዜው አቶ ዳውድን ተክተው የግንባሩን ሥራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ ዳውድ የሥራ ድክመት ኖሮባቸው አሊያም በሌላ ምክያት ሳይሆን አሁን ላይ ሥራቸውን መስራት ባለመቻላቸው ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አቶ ቀጀላ ሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ሥራቸውን ማከናወን ስለማይችሉ ይበሉ እንጅ የማይችሉበትን ምክንያትና የገጠማቸውን አሁናዊ ሁኔታ አልገለጹም፡፡
በትናንትናው ዕለት ከአል ዐይን ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ ቀጀላ የአቶ ዳውድ መኖሪያ ቤት ለደህንነታቸው ሲባል በመንግስት ጥበቃ ሥር መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡