“የዓድዋ ልጆች መሆናችንን ረስተው በአጎአ ሊያስፈራሩን ሞከሩ”- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በአዲስ አበባ መከላከያን የሚደግፍ እና ህወሓትና ሸኔን የሚቃወም ሰልፍ ተካሄደ
ሰልፈኞቹ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እንዲያቆሙ ጠይቀዋል
ህወሓት እና ሸኔን የሚያወግዝ እና የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል
ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ታድመዋል
በሰልፉ ላይ የታደሙ ነዋሪዎችም የተለያዩ መፈክሮችን ይዘው የወጡ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ፤ “የድላችን ሚስጥር ፍትህ ፣ሀቅና እውነት ናቸው፤ ለውጭ ጫና የሚበረከክ ማንንት የለንም፤ የአብሮነት ጉዟችን በሽብርተኞች አይደናቀፍም፤ በመራር ትግል ጣፋጭ ድልን እንቀዳጃለን” የሚሉ ተጠቃሽ ናቸው።
በተጨማሪም አንዳንድ ዓለም አቀፍ መጋናኛ ብዙሃን እና የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እንዲያቆሙ የሚጠይቁ መልክቶችም ተንፀባርቀዋል
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሰልፉ ላይ ባስተላፉት መልእክትም፤ “ምዕራባውያን ከሀገርን ለማፍረስ ከሚሰሩ አሸባሪዎች ጋር በመተባበር አዲስ ምዕራፍ በጀመርንበት ማግስት ጦርነት ከፍትውብናል” ብለዋል።
“ሀገራቱ ሚዲያቸውን በማዝመት የውሽት ዜና በማሰራጨት ሀገር ለማፍረስ እየተረባረቡ ነው” ያሉት ከንቲባዋ፣ “በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል ቢሉም በራሳቸው አካል ውሸት መሆኑ ተረጋግጧል” ብለዋል።
"እንደ ኢትዮጵያ ተልቀን የምንሰጣት ምላሽ ለጠላት መርዶ ለወዳጆች የምሥራች ነው" ያሉት ከንቲባዋ፣ ለኢትዮጵያ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት በነቂስ ወጥቶ በአደባባዩ በመገኘቱ ምስጋና አቅርበዋል።
“የህወሓትቡድን ትላንት ያደረገው ጥፋት ሳያንሰው ዛሬ እንደገና አዲስ ምዕራፍ በከፈትንበት ቀን ጦርነት ከፍቶብናል” ሲሉም ከንቲባዋ ተናግረዋል።
“ተላላኪው ሸኔ እና ሌሎች እሱ የሚጋልባቸውም ዘውምተውብናል፤ ቅኝ መግዛት ተመኝተው ያልተሳካላቸው ዛሬ አንድ ላይ አድመውብናል" ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ “ኢትዮጵያውያን በአንድነት ከቆምን የእነርሱ አድማ ከንቱ ነው፤ ሀገራችንን ማፈራረስ አይችልም” ብለዋል።
"የተመኙት አይሳካም” ያሉት ከንቲባ ዳነች፤ “የአድዋ ልጆች መሆናችንን ረስተው በአጎአ ሊያስፈራሩን ሞከሩ፤ ዕርዳታ እና ብድር ነፃነታችንን የሚገፍፍ እና የሚያስገብረን ከሆነ በፍፁም አይሆንም “ ብለዋል።