በትግራይ አብይአዲ አካባቢ 3 የደንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ሰራተኞች በተፈጸመባቸው ጥቃት ህይወታቸው አለፈ
ከሟቾቹ ውስጥ አንዷ ስፔናዊ ስትሆን ሁለቱ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ናቸው
መከላከያ ጉዳዩን ለሚያጣራ አካል ደጋፍ በማድረግ በራሱም በጠንካራ ማስረጃ አስደግፎ እንደሚያቀርብ ገልጿል
በትግራይ ክልል አብይአዲ አካባቢ የ3 ደንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ሰራተኞች በተፈጸመባቸው ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።
የደንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ሰራተኞቹ በዛሬው እለት በአሸባሪው የህወሃት መገደላቸውን የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮ/ል ጌትነት አዳነ ማምሻውን ገልጸዋልግለጻቸውን ከሀገር መከላከጻ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
"የህወሃት ታጣቂ ቡድን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ( MSF- Médecins Sans Frontières ) የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሰራተኞችን ከመኪና አስወርዶ እንደገደላቸው ቅድመ መረጃ ደርሶናል" ብለዋል ያሉት ኮ/ል ጌትነት።
ከሟቾቹ ውስጥ አንዷ ስፔናዊ ስትሆን ሁለቱ ደግሞ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውንም አስታውቀዋል
የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አክለውም "በየትኛውም መመዘኛ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ሰዎችን መግደል ተቀባይነት የሌለውና ሰላም ወዳድ ሁሉ ሊያወግዘው የሚገባ ጭካኔ ነው" ብለወሰል።
"መላው የሀገሪቱ ህዝቦችና የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡም ይህን የሽብር ቡድን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ከመከላከያ ጎን እንዲሰለፍና ድርጊቱን በተገቢው አጣርቶ እንዲያወግዝ እንጠይቃለን" ነው ያሉት።
ሰራዊቱ ጉዳዩን ለሚያጣራ አካል ደጋፍ በማድረግ በራሱም በጠንካራ ማስረጃ አስደግፎ እንደሚያቀርብ ገልጸዋል።