ይህ የወርቅ ቅብ የኪስ ሰዓት በ150 ሺህ ፓውንድ መነሻ ዋጋ ለጨረታ ቀርቦ ነበር
በታይታኒክ መርከብ ላይ የተገኘው የኪስ ሰዓት 900 ሺህ ፓውንድ ተሸጠ፡፡
በብዙዎች ተወዳጅ ለሆነው ታይታኒክ ፊልም መነሻ የሆነው የመርከብ አደጋ በፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር 1912 ነበር የተከሰተው፡፡
ይህች መርከብ ከብሪታንያዋ ሳውዛምፕተን በመነሳት ወደ አሜሪካዋ ኒዮርክ በመጓዝ ላይ እያለች ከበረዶ ግግር ጋር በመጋጨቷ ምክንያት ለመስመጥ ተገዳለች፡፡
በመርከቧ ላይ የተሳፈሩ ሰዎች በሚያሳልፏቸው ጉዞዎች ዙሪያ መነሻውን ያደረገ ታይታኒክ የተሰኘ የፍቅር ፊልም ከ27 ዓመት በፊት ለተመልካቾች ለእይታ ቀርቧል፡፡
ካናዳ ታይታኒክን ለመጎብኘት ያቀናችው ሰርጓጅ ጀልባ ፍንዳታ ላይ ምርመራ ከፈተች
በዚህ መርከብ ላይ የተገኘ የወርቅ የኪስ ሰዓት ከዚህ በፊት በጨረታ ተሸጦ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ በድጋሚ የሽያጭ ጨረታ ወጥቶበታል፡፡
ጆን ጃኮብ በተባለ የንግድ ሰው በባለቤትነት ተይዞ የነበረው ይህ የኪስ ሰዓት በ150 ሺህ ፓውንድ ለጨረታ የቀረበ ቢሆንም በ900 ሺህ የእንግሊዝ ፓውንድ መሸጡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ጨረታውን ያሸነፈው አካል ይህን የወርቅ የኪስ ሰዓት ከነ ታክሱ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ መክፈል እንደሚጠበቅበት ተገልጿል፡፡
ይህ የወርቅ የኪስ ሰዓት አሁን የተሸጠበት ዋጋ ከመነሻ ዋጋው ጋር ሲነጻጸር በስድስት እጥፍ ጨምሮ መሸጡ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡