ስፖርት
የወርቅ ሜዳሊያ ለሚያመጡ አትሌቶቶቻቸው ከፍተኛ ማበረታቻ ገንዘብ የሚከፍሉ ሀገራት
ሲንጋፖር አትሌዮቿ ለሚያመጡት እያንዳንዱ የወርቅ ሜዳሊያ 475 ሺህ እሸልማለሁ ብላለች
ኢንዶኔዥያ 300 ሺህ እንዲሁም እስራኤል ደግሞ 271 ሺህ እንደምትከፍል አስታውቃለች
የወርቅ ሜዳሊያ ለሚያመጡ አትሌቶቶቻቸው ከፍተኛ ማበረታቻ ገንዘብ የሚከፍሉ ሀገራት
በየ አራት አመቱ አንዴ የሚካሄደው የፓሪስ ኦሎምፒክ ሲካሄድ ስምንተኛ ቀኑን ይዟል።
በውድድሩ ላይ እየተሳታፉ ያሉ ሀገራት አትሌቶቻቸውን ለማበረታታት የገንዘብ ሽልማት አዘጋጅተዋል።
እስያዊቷ ሲንጋፖር ሜዳሊያ ለሚያመጡ አትሌቶቿ ከፍተኛ ገንዘብ እንደምትሸልም አስታውቃለች።
ሀገሪቱ ወርቅ ለሚያመጡ 475 ሺህ ዶላር፣ ብር ለሚያመጡ 373 ሺህ እንዲሁም የነሀስ ሜዳሊያ ለሚያመጡ ደግሞ 168 ሺህ ዶላር እሸልማለሁ ብላለች።
ኢንዶኔዥያ የወርቅ ሜዳሊያ ለሚያመጡ አትሌቶቿ 300 ሺህ ዶላር እንዲሁም እስራኤል ደግሞ 271 ሺህ ዶላር እንደምትሸልም አስታውቃለች።
ካዛኪስታን፣ ማሌዢያ እና ስፔን ሜዳሊያ ለሚያመጡ አትሌቶቻቸው የማበረታቻ ሽልማት እንሰጣለን ካሉ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።