የእስሩ የተባሰው ኪንዛል እና ዚክሮን የተሰኙት ሚሳኤሎች በዩክሬን ተመተው ከወደቁ በኋላ ነው
ሩሲያ ለምን የሚሳኤል ጠበብቶቿን በሀገር መክዳት ወንጀል ጠረጠረች?
በዘመናዊ የጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂ ውድድር በተጧጧፈበት በአሁኑ ወቅት ሩሲያ የሚሳኤል ቴክኖሎጂ ጠበብቶቿን እያሰረች ትገኛለች፡፡
ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ ሩሲያ 12 ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂ ተመራማሪዎችን ያሰረች ሲሆን አንዳንዶቹ በእስር ቤት እያሉ ህይወታቸው አልፏል፡፡
ዩክሩን አሜሪካን ጨምሮ ከኔቶ አባላት በየጊዜው በምታገኛቸው የጦር መሳሪያዎች የሩሲያን ጥቃት ለመመከት እየሞከረች ሲሆን ሞስኮም ያሏትን አዳዲስ ጦር መሳሪያዎች እየሞከረች ትገኛለች፡፡
ኪንዛል እና ዚክሮን የተሰኙት ሚሳኤሎች የትኛውም ሀገር እንዳልታጠቀው ፕሬዝዳንት ፑቲን የተናገሩ ሲሆን ሚሳኤሎቹ ወደ ዩክሬን ከተተኮሱ በኋላ ተመተው እንዲወድቁ ተደርገዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ነበር የሩሲያ ብሔራዊ ደህንነት ከሚሳኤሎቹ መመታት ጀርባ ሚስጢር ተላፎ ተሰጥቷል በሚል የጦር መሳሪያ ጠበብቶች መታሰር የተጀመረው፡፡
በቅርቡ ለእስር ከተዳረጉ የሚሳኤል ቴክኖሎጂ ተመራማሪዎች መካከል ቭላዲስላቭ ጋልኪን እና አናቶሊ ማስሎቭ ዋነኞቹ ሲሆን ማስሎቭ ከአንድ ወር በፊት በተካሄደ ችሎት የ14 ዓመት እስር ተላልፎባቸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሩሲያ አሜሪካ እና አውሮፓ በረጅም ርቀት ሚሳኤሎች እንዲመቱ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ልታደርግ እንደምትችል ገለጸች
ተመራማሪዎቹ እንዳሉት እኛ የሀገርን ጥቅም የሚጎዳ ሚስጢር ለማንኛውም ተቋምም ሆነ ሀገር አሳልፈን አልሰጠንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ እንዳሉት በዓለም አቀፍ የሳይንሳዊ ምርምር ውጤቶች በሚጋሩባቸው ተቋማት የተለመደ እና ሚስጥር ያልሆኑ ሀሳቦቻችንን ከማጋራት ውጪ የተላፉት ህግ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡
ከታሰሩ 12 የጦር መሳሪያ ተመራማሪዎች ውስጥ ሶቱ በእስር ቤት እያሉ ህይወታቸው እንዳለፈም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡