ህወሓት ጊዜያዊ አስተዳሩንና መከላከያን ተባብራቹኋል ያላቸው ንጹሃን ላይ ግድያ እየፈጸመ ነው- መንግስት
ቡድኑ የመከላከያን ከመቀሌ መውጣት ተከትሎ በክልሉ ነዋሪዎች ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን እያደረሰ ይገኛልም ብሏል
መንግስት የተኩስ አቁም በማወጅ መቀሌን መልቀቁን ተከትሎ የህወሓት ሀይሎች በርካታ አካባቢዎች ተቆጣጥረዋል
ህወሓት በመቀሌ እና በሌሎች ከተሞት ጊዚያዊ አስተዳሩ እና መከላከያን ተባራችኋል ያላቸውን ንጹሃን ላይ ግድያ እየፈጸመ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
ህወሓት የመከላከያን ከመቀሌ መውጣት ተከትሎ መቀሌ እና በሌሎች የትግራይ ከተሞች በመግባት በክልሉ ነዋሪ ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን እያደረሰ ይገኛል እንደሚገኝም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
“በመቀሌ እና በሌሎች ከተሞት ከጊዚያዊ አስተዳሩ እና መከላከያን ተባራችኋል ያላቸውን ንጹሃን ላይ ግድያ እየፈጸመ” ነው ያለው መግለጫው፤ ይህንም ተግባሩ የትግራይ ያለውን የሰብዓዊ አቅርቦቶች እጥረት አባብሶ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው ብሏል።
በተጨማሪም ቡድኑ መንግስት ያደረገውን አይነት የተኩስ አቁም ከማድረግ ይልቅ የኢትዮጵያን እና የአለማቀፉን ማህበረሰብ በሃሰተኛ የድል ፕሮፓጋንዳዎቹ ለማታለል እየሰራ ይገኛልም ብሏል።
ህወኃጽ ትኩረት ለማግኘት በሚያደርገው መፍጨርጨር የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪዎችንና የዜጎች ደህንነት በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እያስገባ እንደሆነም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ መንግስት በትግራይ የጀመረውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ መረጃዎችን ለህዝቡ የሚያድርስ የመንግስት የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ ነው።
የፍደራሉ መንግስት ከሰኔ 21 ቀን 2013 ጀምሮ የሚተገበር የተናጠል ተኩስ አቁም በትግራይ ክልል ማወጁን ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም የህወሓት ሀይሎች መቀሌ ከተማን እና ልሎች ትግራይ ክልል አካባቢዎችን መያዛቸውም ይታወቃል።
የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ እና ተለዋጭ አባላት በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ባሳለፍነው አርብ ውይይት ማድረጉም ይታወሳል።
በውይይቱም የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት(ተመድ) የህወሓት ኃይሎች የኢትዮጵያ መንግስት ለጣለው ተኩስ አቁም እንዲገዙና “በአስቸኳይና ሙሉ በሙሉ” እንዲደግፉት አሳስቧል።
የኢትዮጵያ መንግሰትም የትግራይን ቀውስ ለመፍታ ሰላማዊ መንገድን የሚመርጡ የህወሓት አባላትን ጨምሮ ሁሉንም ያካተተ ውይይት ለማድረግ መዘጋጀቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ባሳለፍነው ሳመንት ግልጸው ነበር።