ህወሓት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ እየተደራደረ ነው መባሉን አስተባበለ
ህወሓት ገዥውን ብልፅግና ፓርቲ ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ የሚሉ በስፋት ተሰራጭተዋል
ህወሓት ከብልፅግና ጋር ለመቀላቀል እየተደራደረ ነው በሚል የሚናፈሰው መረጃ “ከእውነት የራቀ ነው” ብሏል
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ እየተደራደረ ነው መባሉን አስተባበለ።
ህወሓት ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመዋሀድ ድርድር መጀመራቸውን የሚጠቁሙ ዘገባዎች ከትናንት ጀመሮ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት ሲዘዋወሩ ነበር።
- የፌደራል መንግስት እና ህወሃት የፖለቲካ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ
- ጠ/ሚ ዐቢይ እና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኙ
ይህንን ተከትሎም ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው አጥር ያለ መግለጫ፤ “ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላልቀል ውይይት አላደረግኩም” ብሏል
ህወሓት አክሎም ከብልጽግና ጋር የሚያደርገው ድርድር ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ለማስፋትና ለማጠናከር ያለመ መሆኑንም አስታውቋል።
በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና በብልጽግና ፓርቲ መካከል መሠረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት እንዳለም ነው መግለጫው ያመለከተው።
ሆኖም ግን ህወሓት ልዩነታቸው እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች እንዳሉም አመልክቷል።
ሆኖም ግን “ህወሃት ከብልጽግናፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ድርድር እያደረገ ነው በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ “ከእውነት የራቀ ነው» ሲል ህወሓት መረጃውን አስተባብሏል።
ገዥው ፓርቲ ብልጽግና ፓርቲ እና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/ ፖለቲካዊ ውይይት ማድረግ መጀመራቸው መነገሩ ይታወሳል።
የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ፖለቲካዊ ውይይቱን ማስጀመራቸውም ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም ከሳምንታት በኋላ በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና አቶ አደም ፋራህ የተመራው የልኡክ ወደ መቀሌ ከተማ በማቅናት ከህወሓት አመራሮች ጋራ ተወያይቷል።