
“ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነው” ብለዋል ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን “ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን ነው" ሲሉ ወርፈዋል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ በተባለው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን “ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው" ብለዋል።
ትራምፕ “ትሁቱና ውጤታማ ኮሜዲያን ዘለንስኪ አሜሪካን 350 ቢሊየን ዶላር በማስውጣት መጀመር ያልነበረባቸው እና የማያሸንፉት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል” ብለዋል።
“ዩክሬን ጦርነቱን ያለ አሜሪካ እና ትራምፕ በፍፁም መቋቋም አትችልም” ሲሉም ገልጸዋል።
ዜለንስኪ ከላክንለት ገንዘብ ግማሹ "የጠፋ" መሆኑን አምኗል ያሉት ትራምፕ “ምርጫ ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለም፣ በዩክሬን የሕዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት በጣም ዝቅተኛ ነው” ብለዋል።
“ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር” ሲሉም ገልጸዋል።
“ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል፤ ካልሆነ ግን የሚያተርፈው ሀገር አይኖርም” ብለዋል ትራምፕ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አክውም "ዩክሬንን እወዳለሁ፣ ነገር ግን ዘለንስኪ አስከፊ ስራ ሰርቷል፣ ሚሊዮኖችም ያለምክንያት ሞተዋል እየሞቱም ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ “ዶናልድ ትራምፕ የሀሰት መረጃ ውስጥ እየኖሩ ወይንም በሀሰት መረጃ እየተነዱ ነው” ብለዋል።