“ዘለንስኪ በኦቫል ቢሮ ውስጥ ትክክለኛ በጥፊ የተቀበለ ተሳዳቢ ነው”- ዲሜትሪ ሜድቬዴቭ
ሩሲያ በትራምፕ-ዘለንስኪ ግጭት ዙሪያ ደስታ የተሞላበት ምላሽ ሰጥታለች

ማሪያ ዛካሮቫ “ትራምፕና ምክትላቸው ቫንስ ዘሌንስኪን ከመምታት መቆጠባቸው ተአምር ነበር” ብለዋል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ በዋይት ኃውስ ያደረጉት ውይይት ወደ ቃላት ግጭት መግባን ተከትሎ የሩሲያ ባለስልጣና አስተያየት እየሰጡ ነው።
ሞስኮ አርብ ዕለት በዋይት ሀውስ በዶናልድ ትራምፕ እና በቮሎዲሚር ዘለንስኪ መካከል ለተፈጠረው ግጭት ደስታ የተሞላበት ምላሽ ሰጥታለች።
የሩሲያ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የሩሲያ የፀጥታ ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ ዲሜትሪ ሜድቬድቭ፤ ክስተቱን “ተሳዳቢው አሳማ በኦቫል ቢሮ ውስጥ ትክክለኛ በጥፊ ተቀበለ” ሲሉ ገልጸዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በበኩላው፤ “ፕሬዝዳንት ትራምፕና ምክትላቸው ቫንስ ዘሌንስኪን ከመምታት መቆጠባቸው ተአምር ነበር” ብለዋል።
ዛካሮቫ “ዘሌንስኪ ከትራምፕ ጋር ባደረገው ንግግር ላይ እኳን ብዙ ውሸቶችን ተናግሯል፤ ለዚህም ቁጣ እና የቃል ዘለፋ ብቻ ሳይሆን ቡጢም ይገባው ነበር” ብለዋል።
የክሬምሊን የቀድሞ አማካሪ ሰርጊ ማርኮቭ፤ የወይት ኃውስ ክርክር የዜሌንስኪን የፖለቲካ ዘመን የሚያፋጥን ነው ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ በዋይት ኃውስ ያደረጉት ውይይት ወደ ቃላት ግጭት አምርቶ ያለ ምንም ስምምነት መጠናቀቁ ይታወሳል።
በዋየት ኃውስ በኦቫል ፅህፈት ቤት በነበራቸው ቆይታ ዶናድ ትራምፕ ቮሊድሚር ዜልኒስኪን “አክብሮት የጎደለው ባህሪ” ከሰዋል።
በንግግራቸው ወቅትም ትራምፕ ዘሌንስኪን “በሚሊየኖች ህይወት እና በ3ኛ የዓለም ጦርት ቁማር እየተጫወትክ ነው” ብለዋል።
ዘለንስኪ የሰለም ስምምነት ለመፈረም ዋስትና ያስፈልገናል ቢሉም፤ ትራምፕ "ለመደራደሪያ የሚሆን አቅም እና ሥልጣን የለህም" በማለት አቋርጠዋቸው ያለህ አማራጭ ስምምነቱን መፈረም ነው ካልሆነ አሜሪካ ከዚህ ትወጣለች” ሲሉም ተናግረዋል።
ይህንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ዋይት ሀውስን ጥለው የወጡ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ሊያደርጉት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫም ተሰርዟል፡፡