ሁለት ተጨማሪ እህል የጫኑ መርከቦች ከዩክሬን ወደብ ተንቀሳቀሱ
ከስምምነቱ በኋላ እስካሁን 16 መርከቦች እህል ጭነው ከዩክሬን የብላክ ሲ ወደቦች ተንቀሳቅሰዋል
ሩሲያ፣ ቱርክ እና ተመድ ከዩክሬን ወደቦች እህል እንዲንቀሳቀስ መስማማታቸው ይታወሳል
ከዩክሬን ብላክ ሲ ወደብ እህል የጫኑ ሁለት መርከቦች መንቀሳቀሳቸውን የቱርክ መከላከያ ሚኒስትቴር ማስታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሩሲያ፣ ቱርክ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ከዩክሬን ወደቦች እህል እንዲንቀሳቀስ በተስማሙት መሰረት እስካሁን እህል ጭነው ከዩክሬን የወጡ መርከቦች ቁጥር 16 ደርሷል፡፡
የቱርክ መከላያ ሚኒስቴር 12 ሺ ቶን በቆሎ የያዘችመ የባርባዶስ ባንዲራ የሰቀለች መርክብ ከዩክሬኑ ቾርኖሞርስክ ወደብ ተንቀሳቅሳ ወደ ደቡባዊ ቱርክ እያመራች መሆኑን አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ በተመሳሳይ ሌላ የባርባዶስ ባንዲራ የምታውለበልብ መርከብ 3 ቶን ሱፍ ጭና ወደ ቱርኳ ቲከርዳ ግዛት ማምራታን ገልጿል፡፡
ሌላ የቱርክ መርከብ እህል ለመግዛት ወደ ዩክሬን መንቀሳቀሷን ሚኒስቴሩ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡
የዩክሬን የመሠረተ ልማት ሚኒስቴር ቅዳሜ እንዳስታወቀው 450,000 ቶን የግብርና ምርቶችን የያዙ 16 መርከቦች ከዩክሬን ባህር ወደቦች ከነሐሴ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ለመርከቦች ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መሄዳቸውን አረጋግጧል።
ዩክሬን የእህል ምርቷን ወደ አፍሪካ እና ወደ ሌሎች ሀገራት የምታስወጣበት የብላክ ሲ ወደብ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት መዘጋቱ በተለይም በአፍሪካ የምግብ እህል አቅርቦት እንዲያጋጥም አድርጎ ነበር፡፡ ተመድ ከቱርክ እና ከሩሲያ ጋር ባደረገው ስምምነት ምክንያት ሩሲያ በብላክ ሲ ላይ የጣለችውን ከበባ እንድታነሳ መስማማቷ ይታወሳል፡፡