ከፍተኛ የተመድ ባለስልጣናትን በአድሎአዊነት የተቹ ሁለት የተመድ ሰራተኞች ከኢትዮጵያ ተጠሩ
መንግስት ለህወሃት ያደላሉ ያላቸውን 7የተመድ ሰራተኞች ማባረሩ ይታወሳል
ተመድ የትችት ድምጽ ቅጅ የተገኘባቸውን ሁለት ሰራተኞቹን ከኢትዮጵያ ወደ ዋና መስሪያቤቱ መጥራቱ ተገለጸ
የተመድን ከፍተኛ ባለስልጣት የሚተች ቅጅ መገኘቱን ተከተሎ በኢትዮጵያ ሲሰሩ የነበሩ ሁለት የተመድ ሰራተኞች መጠራታቸውን የተመድ ፖፑሌሽን ፈንድ ቃል አቀባይ መናገሩን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በተገኘው ቅጅ ሁለት በኢትዮጵያ ለሚገኘው ተመድ እንሰራለን ያሉ ሰራተኞች ስማቸውን ሳይጠቅሱ ለአንድ የፊሪላንስ ጋዜጠኛ አንዳንድ የተመድ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለህወሃት ያዝናሉ ብለው ተናግረዋል፡፡
- ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል ያለቻቸውን 7 የተመድ ሰራተኞች በ72 ሰዓታት ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች
- “ኢትዮጵያ የተመድን ሰራተኞች ለማባረር መወሰኗን በመስማቴ ደንግጫለሁ”-አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
በሰሜን አትዮጵያ በህወሃትና በፌደራል መንግስት መካከል ያለው ግጭት አንድ አመት ሆኖታል፤ ግጭቱ አሁን ላይ በአማራና አፋር ክልል ላይ ሆኗል፡፡ የቅጅውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ እንደማይችል የዘገበው ሮይተርስ፤ በቅጅው ውስጥ የሰራተኛዋ ድምጽ ይሰማል ብሏል፡፡
አለም አቀፉ የሰደተኞች ድርጅት(አይኦኤም) የጻፈውን ደብዳቤ ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ሰራተኞቹ ወደ ተመድ ዋና መስሪያ ቤት እንዲጠሩና ጎንለጎን ምርመራ እንዲደርግባቸው መወሰኑን ያሳያል፡፡
ሮይተርስ አግኝቸዋለሁ ባለው ደብዳቤ መሰረት፤ የአይ ኦኤም ዋና ዳሬክተር ቪቶሪኖ በቅጅው የተደመጠው አስተያየት ከአይኦኤም መርህና አሰራር ጋር አብሮ አይሄድም ብለዋል፡፡ ዋና ዳሬክተሩ በወደ ዋና መስሪያ ቤት የተጠሩትን ሰራተኞች ስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል፡፡
በቅጅው ውስጥ ከተደመጡት ሁለት ሰዎች መካከል አንደኛዋ ሴት በአዲስ አበባ የአይኦኤም ተወካይ ማውሪን አችንግ ናቸው፡፡ ተመድ ኤችንግ አስገዳጅ እረፍት እንዲወጡ አድርጓል፡፡
ሮይተርስ ወደ ዋና መስሪያ ቤት የተጠሩት ማውሪን አችንግ ናቸው ውይ ብሎ ቢጠይቅም መልስ አለማግኘቱን ዘግቧል፡፡ ዘገባው ጋዜጠኛውንም ሆነ አችንግን ማግኘት አለመቻሉን ጠቅሷል፡፡ በቅጅው ውስጥ ድምጻቸው የተሰማው ሌላው የተመድ ሰራተኛ ደግሞ የተመድ ፖፑሌሽን ፈንድ የኢትዮያ ተወካይ ዲኒያ ጋይሌ ናቸው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት አንድ አመት ባስቆጠረው ግጭት ውስጥ የተመድ ሰራተኞች፣ከመደበኛ ስራቸው ውጭ በመንቀሳቀስ ህወሃት እየረዱ የሚል ክስ ሲያሰማ ቆይቷል፡፡ መንግስት በቅርቡ ሰባት የተመድ ሰራተኞችን ማስወጣቱ ይታወሳል፡፡ ተመድ ኢትዮጵያ ውሳኔዋ ተቃውል፣ውሳኔው እንዲቀለበስም በወቅቱ ጠይቋል፡፡