“ኢትዮጵያ የተመድን ሰራተኞች ለማባረር መወሰኗን በመስማቴ ደንግጫለሁ”-አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
የ3 ቀኑ አስቸኳይ ማሳሰቢያ ከተሰጣቸው መካከል አንዷ የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አዴል ኮድር ናቸው
ጉቴሬዝ ሰራተኞቹ በኢትዮጵያ መስራታቸውን በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ ከመንግስት ጋር በመነጋገር ላይ ነን ብለዋል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኢትዮጵያ የድርጅቱን ከፍተኛ ሰብዓዊ አስተባባሪዎች ጨምሮ ሰባት የድርጅቱን ሰራተኞች ለማባረር መወሰኗን በመስማቴ ደንግጫለሁ ሲሉ አስታወቁ፡፡
ዋና ጸሃፊው ሁኔታውን በማስመልከት በቃል አቀባይ ጽህፈት ቤታቸው በኩል መግለጫ አውጥተዋል፡፡
የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት(ኦቻ) “የተዛቡ መግለጫዎች ከመስጠት እንዲቆጠብ” ኢትዮጵያ ጠየቀች
በመግለጫው “ኢትዮጵያ የድርጅቱን ከፍተኛ ሰብዓዊ አስተባባሪዎች ጨምሮ ሰባት የድርጅቱን ሰራተኞች ለማባረር መወሰኗን በመስማቴ ደንግጫለሁ” ነው ያሉት፡፡
ሁሉም ሰብዓዊ ተግባራት በሰብዓዊነት፣ ያለ አድልዖ፣ በነጻ እና ገለልተኛነት መርሆዎች የሚመሩ ናቸው ያሉ ሲሆን ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒቶችን ጨምሮ ህይወት አድን ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
በሰብዓዊ ጉዳዮች ስም ኢትዮጵያ ጫና እንዲበረታባት አድርገዋል በሚል የሚወቀሱት የተመድ ሰብዓዊ አስተባባሪ ስልጣን ለቀቁ
“ይህን በሚሰሩ የኢትዮጵያ ስታፍ አባላት ሙሉ መተማመን አለኝ” ም ነው ጉቴሬዝ በመግለጫው ያሉት፡፡
ድርጅታቸው ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ሰራተኞቹ ስራቸውን በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውንም ዋና ጸሃፊው አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብተዋል ያለቻቸውን ሰባት የድርጅቱን ሰራተኞች በ72 ሰዓታት ሃገሪቱን ለቃችሁ ውጡ ስትል ማሳሰቧ የሚታወስ ነው፡፡
አስቸኳይ ማሳሰቢያው ከተሰጣቸው መካከል አንዷ የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አዴል ኮድር ናቸው፡፡