አሜሪካ ፤ ለዩክሬን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ያከተተ ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች
የአሜሪካ-ዩክሬን ትብብር ይበልጥ ለማጎልበት የአሜሪካ ልዑካን ወደ ኪቭ እንደምትመልስ አስታውቃለች
ጉብኝቱ ከሩሰያ-ዩክሬን መጀመር ወዲህ በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ የተደረገ የመጀመሪያው ጉብኝት መሆኑ ነው
አሜሪካ፤ ለዩክሬን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ያከተተ ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች።
አሜሪካ ይህንን የአጋርነት ማረጋገጫ ቃል የሰጠችው፤ በትናንትናው እለት በዩክሬን ጉብኝት ባደረጉት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን አማካኝነት ነው።
ሚኒስትሮቹ ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በአሁናዊ የዩክሬን ሁኔታ ዙርያ ውይይት ማድረጋቸውም የፕሬዝዳንቱ አመካሪዎች ገልጸዋል።
ውይይቱ ተከትሎም፤ ዩክሬን የገጠማትን ፈተና በድል እንድትወጣ ያግዝ ዘንድ አሜሪካ ለዩክሬንና ለሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) 713 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቷ ይፋ ተደገርጓል።
ከዚህ ድጋፍ ውስጥ ግማሹ ለዩክሬን የሚሰጥ ሲሆን ቀሪው ግማሽ ደግሞ የኔቶ አባል ሀገራት እንዲሁም ለዩክሬን ድጋፍ እያደረጉ ያሉ ሀገራት እንደሚከፋፈሉት አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።
የአሜሪካ-ዩክሬን ትብብር ይበልጥ ለማጎልበት፤ የአሜሪካ ልዑካን ወደ ኪቭ ይመለሳሉም ብለዋል ሚኒሰትሮቹ።
ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ 165 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ ተተኳሾችን ለዩክሬን ለመሸጥ ዝግጁ ነች ተብሏል።
የሚኒስትሮቹ የኪቭ ጉብኝት ሩሰያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ ከጀመረች ወዲህ በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ የተደረገ የመጀመሪያው ጉብኝት ነው ተብሎለታል።
በትናንትናው እለት ስለ ጉብኝቱ መረጃ ከመስጠት የተቆጠበው ኋይት ሀውስ አሁን ላይ ብሊንከን እና የኦስቲን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ከዩክሬን ግዛት መውጣታቸውን አስታውቋል።
በሌላ በኩል የጀርመን ምክትል ቻንስለር ሀገራቸው ቀደም ብላ ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ ማድረግ አለመጀመሯ ስህተት እንደሆነ ተናግረዋል።
ሮበርት ሃቤክ ከአንድ የጀርመን የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቆይታ ጀርመን ለዩክሬን የምታደርገው ድጋፍ ከዓመታት በፊት መጀመር ነበረበት ሲሉ ተደምጠዋል።
''በእርግጠኝነት በጣም ቀደም ብለን ዩክሬንን መደገፍ ነበረብን፤ ይህንን ስል ከቀናት፣ ሳምንታት አልያም ወራት በፊት እያልኩ አይደለም፤ ከዓመታት በፊት ነበር የድጋፍ እጃንን መዘርጋት የነበረብን''ብለዋል።
aXA6IDMuMTQ0LjI1My4xNjEg
ejasoft island