አረብ ኢሚሬትስ ለተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነት እንደምትወዳደር አስታወቀች
አረብ ኢሚሬትስ በፈረንቹ 2028 እስከ 2030 የቆይታ ዘመን የምክር ቤቱ አባል ለመሆን ዕጩ መሆኗን ይፋ አድርጋለች

አረብ ኤሚሬትስ ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበርና ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አስታውቃለች
የተባሩት አረብ ኢምሬትስ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነት እንደምትወዳደር አስታወቀች።
አረብ በፈረንቹ 2028 እስከ 2030 የቆይታ ዘመን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ለመሆን ዕጩ መሆኗን ይፋ አድርጋለች።
የአረብ ኤሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ ኑራ አል ካቢ በጄኔቫ በተካሄደው 58ኛው የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው የአረብ ኢምሬትስን እጩነት ይፋ ያደረጉት።
አል ካቢ በንግግቸው “አረብ ኢምሬትስ በአለም ዙሪያ ያሉ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ለመፍታት ከሁሉም ሀገራት ጋር በምክር ቤቱ ማዕቀፍ ውስጥ ለመስራት ፍላጎት አላት” ሲሉ ገልጸዋል።
አረብ ኤሚሬትስ ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበርና ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ገልጸው፤ ለሰብአዊ መብቶች መሻሻልና ማስተዋወቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ በርካታ መርሃ ግብሮችንና ቀርጻ እየሰራች መሆኑን አስታውቀዋል።
ሚኒትር ደኤታዋ አክለውም፤ አረብ ኢሚሬትስ የሰብአዊ መብቶችን እና መሰረታዊ ነፃነቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እና ለማረጋገጥ ብሄራዊ ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን ቀርጻ አሰራር መዘርጋቷም ገልጸዋል።
አል ካቢ፤ አረብ ኢሚሬትስ 2025ን "እጅ ለእጅ" በሚል መሪ ቃል የህብረተሰብ አመት እንዲሆን ወስና እየሰራች አንደሆነም አንስተዋል።
አረብ ኤሚሬትስ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የ3 ዓመት አባልነት ምክር ቤቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የሰብአዊ መብቶችን በማስተዋወቅ እና በመጠበቅ ረገድ ጠቃሚ እና ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው እምነት እንዳላት አፅንዖት ሰጥቷል።
አረብ ኤሚሬትስ ከ200 በላይ ሀገራት ዜጎች በመቻቻልና በመተሳሰብ የሚኖሩባት ሀገር መሆኗ ያወሱት አል ካቢ፤ ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር እና ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት የምትሰራ እንዲሁም ቀልጣፋና ፍትሃዊ የፍትህ ስርአት ባለቤት መሆኗን አስረድተዋል።
አረብ ኤሚሬትስ ለሶስት ጊዜ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል የምትሆን ከሆነ ኩራት እንደሚሰማት ሚኒስር ደኤታዋ አስውቀዋል።
አል ካቢ፤ “አረብ ኢሚሬትስ ከ2028 እስከ 2030 ለሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነት እጩ መሆኗን ሳበስር ደስታ ይሰማኛል” ያሉ ሲሆን፤ “በአለም ዙሪያ ያሉ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ለመፍታት ከሁሉም ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት በጉጉት እንጠብቃለን” ብለዋል።