የዮርዳኖስ ንጉስ አብዱላህ ሁለተኛ አዘውትሮ ኤሚሬትስን በመጎብኘት ይታወቃሉ
የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የዮርዳኖሱ ንጉስ አብዱላህ ኢብን አል ሁሴን በሁለቱ ሀገራት ወንድማማችነት እና ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል።
ይህ የሆነው ፕሬዝደንት ሼክ መሀመድ በአቡዳቢ በአል ሻቲ ቤተ-መንግስት ንጉስ አብዱላሂን ሲቀበሉ ነው።
- አረብ ኢሚሬትስ፣ ግብጽ እና ዮርዳኖስ “አዲስ የኢኮኖሚ ትብብር ምእራፍ ነው” የተባለለት ስምምነት ተፈራረሙ
- አረብ ኢሚሬትስ በውጭ ንግድ በዓመቱ መጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት የ19 በመቶ እድገት ማስመዝገቧ ገለጸች
የዮርዳኖስ ንጉስ “የወንድማማችነት ጉብኝት” በተባለው ጉዞ በከፍተኛ ባለስልጠናትና በበርካታ ሼኮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል አቡሳቢ ገብተዋል።
በውይይቱ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ አል ናህያንን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት መገኘታቸውን የኤምሬትስ ዜና ወኪል ዘግቧል።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ እና ዮርዳኖስ ጠንካራ የግንኙነት ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ የዮርዳኖስ ንጉስ አብዱላህ አዘውትሮ ኤሚሬትስን ይጎበኛሉ።
ሼክ ሞሃመድ እና ንጉስ አብዱላህ በሰኔ ወር በአቡ ዳቢ ውይይት አድርገው በፖለቲካ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት መስኮች ትብብርን ለማዳበር ያሉ እድሎችን መገምገማቸው ተነግሯል።
ሁለቱም ሀገራት ትናንት ዕሮብ በእየሩሳሌም አል-አቅሳ መስጊድ ግቢ ውስጥ የተፈጠረውን ክስተቶች “የዓለም አቀፍ ህግን መጣስ” ሲሉ አውግዘዋል።