ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አረብ ኢምሬትስ ለዩክሬኑ ቀውስ ሰላማዊ መፍትሄ የሚያመጡ ጥረቶች እንደምትደግፍ ገለጹ
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በአረብ ኢምሬትስ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ካለት የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር ተወያይተዋል

አረብ ኢምሬትስ ሩሲያና ዩክሬን የጦር ምርኮኞችን እንዲለዋወጡ አደራድራለች
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ቬክ መሀመድ ቢን ዛይድ አረብ ኢምሬትስ ለዩክሬኑ ቀውስ ሰላማዊ መፍትሄ የሚያመጡ ማንኛቸውንም ጥረቶች እንደምትደግፍ ገልጸዋል።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ይህን ያሉት በአረብ ኢምሬትስ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ካለት የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።
ለቀጣናውና ለአለም ሰላም ሲባል የዩክሬኑ ቀውስ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚደረገውን ጥረት እንደምትደግፍ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ገልጸዋል።
ሰብአዊ ቀውሶችን የመቀነስ ጥረቷን እንደምትገፋበት የገለጹት ፕሬዝደንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ለዩክሬኑ ቀውስ ሰላማዊ መፍትሄ የሚያመጡ ማንኛቸውንም እንቅስቃሴዎች እንደምትደግፍ በአጽንኦት ተናግረዋል።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ዘለንስኪ አረብ ኢምሬትስ የዩክሬንና የሩሲያን የጦር እስረኞች ለማለዋወጥ ያደረገችው ጥረት እንዲሳካ በማድረጋቸው ምስጋና ችረዋቸዋል።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪም በሁለቱ ሀገራት መካከል ትብብር ሊደረግባቸው የሚችሉ በርካታ እድሎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።ፕሬዝደንት ዘለንስኪም አረብ ኢምሬትስ የጦር እስረኞችን በማለዋወጥ ያደረጉትን ጥረት አድንቀዋል።
መሪዎቹ ከዩክሬኑ ጦርነት በተጨማሪ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን በማጠናከር ጉዳይ ተወያይተዋል።
ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ በወይይቱ ወቅት ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ትብብር ያጠናክረዋል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል። ፕሬዝደንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድና ፕሬዝደንት ዘለንስኪ የሁለቱ ሀገራት የልማት ትኩረቶች በሆኑት በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ዋስትና እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በመላው አለም ካሉ ወዳጅ ሀገራት ጋር የሚደረግ ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጡ በአጽንኦት ተናግረዋል።