ብሪታንያ ታዳጊ ሀገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገሯ እንዲያስገቡ ፈቀደች
የአፍሪካ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ከፈቀዱ የአውሮፓ ሀገራት መካከል ብሪታንያ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች
ብሪታንያ በአጠቃላይ ለ65 የዓለም ታዳጊ ሀገራት ያለቀረጥ ምርቶቻቸውን ወደ ሀገሯ እንዲያስገቡ ፈቅዳለች
ብሪታንያ ታዳጊ ሀገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገሯ እስዲያስገቡ ፈቀደች።
ብሪታንያ ያላደጉ ሀገራት የተለያዩ ምርቶቻቸውን ወደ ሀገሯ ያለቀረጥ እንዲያስገቡ የፈቀደች ሲሆን ሀገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴዋን ለማሳለጥ በሚል እድሉን እንደፈቀደች አስታውቃለች፡፡
በዚህ እድል መሰረት ምርቶቻቸውን ወደ ብሪታንያ እንዲያስገቡ ከተፈቀደላቸው መካከል የአፍሪካ ሀገራት ዋነኞቹ ሲሆን በርካታ ሀገራት ምርቶቻቸውን ያለቀረጥ እንዲያስገቡ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
ብሪታንያ ከሚመጣው ጥር ወር ጀምሮ ታዳጊ ሀገራት ምርቶቻቸውን ወደ ሀገሯ እንዲያስገቡ የፈቀደች ሲሆን ያለቀረጥ ለታዳጊ ሀገራት ምርቶች በራቸውን ከከፈቱ የአውሮፓ ሀገራት መካከል ብሪታኒያ የመጀመሪያዋ መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
አልባሳት፣ጫማዎች፣ የተለያዩ ምግብ እና ምግብ ነክ ምርቶች በተለይም በብሪታንያ በብዛት የማይመረቱ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ በሆነ መንገድ ከታዳጊ ሀገራት ወደ ብሪታኒያ እንዲገቡ የተፈቀዱ ምርቶች ናቸው፡፡
ብሪታንያ በዘረጋችው በዚህ እድል መሰረት አፍሪካን ጨምሮ 65 የዓለማችን ታዳጊ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚሆኑም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
የብሪታንያ ዓለም አቀፍ ንግድ ተቋም እንዳለው ከሆነ ይህ ከቀረጥ ነጻ እድል ብሪታንያ በዓለም ላይ ድህንት እንዲጠፋ ቃል የገባችውን ወደ ተግባር የመቀየሩ ዋነኛ ስራዋ አካል ነው፡፡
እንዲሁም በዓለም ላይ በእርዳታ ላይ የተመሰረቱ ህይወቶችን ለመቀየር የተገባውን ቃል ለመተግበር እና ከአየር ንብረት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ጉዳቶች የመቀነሱ አካልም እንደሆነ ዘገባው አክሏል፡፡
ታዳጊ ሀገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነጻ በሆነ መንገድ ወደ ብሪታንያ እንዲያስገቡ የተፈቀደው የብሪታንያ ኢኮኖሚን ለመደገፍ፣ የኑሮ ውድነቱን ለማስታገስ እና ሌሎች ተያያዥ የኢኮኖሚ ጥቅሞች ሲባልም ነው ተብሏል፡፡