ለቀልድ በሚል የጦር መሳሪያ በሰዎች ላይ የደገኑት አምባሳደር ከሀላፊነት ተነሱ
በሜክሲኮ የብሪታንያ አምባሳደር ከዲፕሎማት የማይጠበቅ ድርጊት ፈጽመዋል ተብሏል
አምባሳደር ጆን ቤንጃሚን ለቀልድ ሰው ላይ ሲደግኑ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ስራቸውን አሳጥቷቸዋል
ለቀልድ በሚል የጦር መሳሪያ በሰዎች ላይ የደገኑት አምባሳደር ከሀላፊነት ተነሱ
ጆን ቤንጃሚን የተሰኙት ዲፕሎማት ከሶስት ዓመት በፊት ነበር በሜክሲኮ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ተደርገው የተሾሙት፡፡
ከሰሞኑ ወደ ሰሜናዊ ሜክሲኮ አቅንተው ለጉብኝት በሄዱበት ወቅት አውቶማቲክ የሆነ ዘመናዊ ጦር መሳሪያ ይዘው በሰዎች ላይ ሲደቅኑ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል፡፡
አምባሳደሩ ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን በተሽከርካሪ እየተጓዙ እያሉ በሰዎች ላይ ሲደቅኑ ሲስቁ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል የብዙዎችን ትኩረት ስቦ ቆይቷል፡፡
የዩናይትድ ኪንግደም መንግስትም አምባሳደር ቤንጃሚንን ከሀላፊነት ያነሳ ሲሆን ምክንያቱን በግልጽ ከመናገር ተቆጥቧል፡፡
የእስራኤል ፍርድ ቤት በአስገድዶ መድፈር የተከሰሱት የቀድሞ ዲፕሎማት ተላልፈው እንዲሰጡ ወሰነ
የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ከአሶሼትድ ፕረስ ለቀረበለት ጥያቄ አምባሳደሩ ስለፈጸሙት ስህተት እናውቃለን ለዚህም ተገቢውን እርምጃ ወስደናል፣ ጉዳዩ በውስጥ የዲፕሎማሲ አሰራራችን አማካኝነት እልባት አግኝቷል ሲል ባጭሩ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
በለንደን የዲፕሎማሲ ማዕከል የተማሩት አምባሳደር ቤንጃሚን ዩናይትድ ኪንግደም ካሏቸው ልምድ ያላቸው ዲፕሎማቶች መካከል አንዱ ናቸው ተብሏል፡፡
አምባሳደሩ ከዚህ በፊት በችሊ፣ ጋና፣ ቱርክ፣ አንዲኔዥያ እና አሜሪካ በተለያዩ ሀላፊነቶች ተመድበው ሲሰሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡