በውሰት ለጋና ከሚመለሱ መካከል የወርቅ ልብስና ጎራዴን ጨምቶ 32 ቅርሶች ይገኙበታል
ብሪታኒያ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከጋና የዘረፈቻቸውን ቅርሶች በውሰት ስምምነት ልትመልስ መሆኑ ተገለጸ።
ብሪታንያ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከአሳንቴ ንጉስ የተዘረፈውን የጋና የወርቅ ልብስ እና ሌሎች ቅርሶችን ለጋና በውሰት ለመመለስ የሚያስችላትን ስምምነት በትናንትናው እለት ደርማለች።
በስምምነቱ መሰረት ብሪታኒያ በ19ኛ ክፍለ ዘመን ከጋና የዘረፈቻቸውን 32 ቅርሶች በውሰት ትመልሳለች የተባለ ሲሆን፤ በውሰት ለጋና ከሚሰጡ ቅርሶች መካከለም የውርቅ ልብስ፣ የወርቅ ጎራዴ እና ሌሎች ከወርቅ የተሰሩ መገልገያዎች ይገኙበታል።
በለንደን ቢሪታኒያ ሙዝየም፣ እንዲሁም በቪክቶሪያ እና ኦልበርት ሙዚየሞች ውስጥ የሚገኙት ቅርሶቹ ከተዘረፉ ከ150 ዓመታት በኋላ ለጋና ማንሂያ ቤተ መንግስት ሙዚየም በውሰት የሚሰጡ ይሆናል።
ቅርሶቹ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በተደረገው የአንግሎ-አሳንቴ ጦርነት ወቅት ከኩማሲ የተዘረፉ በመሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በምዕራብ አፍሪካ ከእንግሊዝ የቅኝ ግዛት ታሪክ ጋር ግንኙነት አላቸው።
ብሪታያ በቀኝ ግዛት ዘመን ከአፍሪካ የዘረፈቻውን በዋጋ የማይተመኑ ቅርሶች እንድትመልስ ከበርካታ ሀገራት ጋር ክርክር ላይ እንደምትገኝም ሮይተርስ ዘግቧል።
የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለብሪታኒያ ጥያቄ ካቀረቡ ሀገራት መካከል ናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ ይገኙበታል።
ይሁን እንጂ አንድ አንድ የብሪታኒያ ሙዚየሞች በእጃቸው የሚገኙ እና ጥያቄ የሚቀርብባቸው አከራካሪ ቅርሶች በቋሚነት እንዳይመለሱ በህግ በመከልከል ላይ ይገኛሉ።