ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል ብትሆን የምታገኝው ጥቅም ምንድን ነው?
ሀገሪቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን የምታደርገው ድርድር በሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራል
ሀገሪቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን የምታደርገው ድርድር በሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራል
ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን የምታደርገው ድርድር በሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ይጀምራል።
የሩሲያን ጥቃት ተከትሎ በሳምንታት ውስጥ የቡድኑ አባል ለመሆን ኬቭ ጥያቄ አቅርባለች፡፡
ረዘም ላለ ጊዜ የሀገሪቱን የአባልነት ጥያቄ ሲያጤን የሰነበተው ህብረቱ ሀገሪቱ አባል በምትሆንበት ሁኔታ የአውሮፓ ህብረት ሚኒስትሮች ድርድር አንዲጀምሩ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡
ከኬቭ በተጨማሪ ሞልዶቫ ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ ድርድር ጎን ለጎን ይካሄዳል ተብሏል፡፡ ሩሲያ በባለፈው አመት ዩክሬን በኢኮኖሚያው ትብብሮች ላይ መሰረት ያደረገውን የአውሮፓ ህብረት ብትቀላቀል እንደማትቃወም ማስታወቋ አይዘነጋም፡፡
በአውሮፓ ህብረት አባልነት ውስጥ መታቀፍ ያለው ጥቅም ምንድን ነው?
ከሩሲያ ጋር የገባችበትን ጦርነት ተከትሎ በድጎማ የሚንቀሳቀስ ኢኮኖሚ የምትመራው ኬቭ ህብረቱን መቀላቀል በ27 ሀገራቱ ስብስብ ውስጥ ተጽእኖው ምን ይሆን የሚለው ከ2022 ጀምሮ በአውሮፓ ፖሊሲ አውጪዎች ሲተነተን የነበረ አጀንዳ ነው፡፡
ምንም እንኳን ዩክሬን በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ እያለፈች ብትገኝም ለህብረቱ የሚኖራት አብርክቶ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡
በአለም ላይ ቀዳሚዋ የጥራጥሬ እህል ላኪ የሆነችው ሀገር ከሰፊ የግብርና ምረቷ ባለፈ በነዳጅ ሀብት እና የተማሩ ዜጎቿ ለህብረቱ አስተዋጽኦ ከምታበረክትባቸው ዘርፎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
በምህንድስና እና ኮምፒውተር ሳይንስ በርካታ ምሁራን ያሏት ሀገሪቱ በአገልግሎት ዘርፍ ወደ አውሮፓ ከምትለከው መካከከል የተማሩ ዜጎቿ 45 በመቶውን ይሸፍናሉ፡፡
የተፈጥሮ ሀብትን በተመለከተ አውሮፓ ለመኪና እና ለሌሎች የፋብሪካ ምርቶች ቻይና ላይ ጥገኛ የሆነባቸው ማዕድናት በዩክሬን ይገኛሉ ፣ እናም ኬቭ የስብስቡ አባል ብትሆን ወደ አውሮፓ የምትልካቸው የተፈጥሮ ማዕድናት ምርት መጠን ስለሚጨምር ህብረቱ ተጠቃሚ ነው፡፡
ባለፉት አመታት በምዕራባዊያን ሀገራት እንደ አጠቃላይ በአለም አቀፍ ደረጃ መረጋጋት ያቃተው የነዳጅ ዋጋ በአውሮፓ ሀገራት የፈጠረውን ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ለማቃለል ከፍተኛ የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችት ባለቤት የሆነችው ዩክሬን አበርክቶ ከፍተኛ ነው፡፡
ኬቭ በአሁኑ ወቅት የምትገኝበት የኢኮኖሚ ሁኔታ ከአውሮፓ ህብረት አንድ በመቶውን አጠቃለይ ሀገራዊ እድገት የሚሸፍን ነው፡፡
በጦርነቱ ከደረሰባት ጉዳት ለማገገም ደግሞ በመጪዎቹ አስርተ አመታት እስከ 400 ቢሊዮን ዶላር የሚያስፈልጋት ሀገሪቱ ለህብረቱ በሚኖራት ኢኮኖሚያዊ አበርክቶ ልክ የምታገኝው ፋይናንሻል ድጋፍ ከፍተኛ የሚሆን ነው፡፡
በተጨማሪም ጦርነቱ ካበቃ በኋላ አባል በመሆኗ ብቻ ወደ ሀገር ውስጥ የምታስባቸው ግዙፍ የአውሮፓ ኩባንያዎች ለኢኮኖሚያዋ መነቃቃት ወሳኝ ናቸው፡፡
የህብረቱ አባል ሀገር ለመሆን በውጭ ጉዳዮችና በኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች ማሻሻል የሚጠበቅባት አሰራሮች አሉ፡፡ ከዚህ ባለፈም በዴሞክራሲያዊ ስርአት ፣ በዜጎች ነጻነት እንዲሁም ሙስናን መቆጣጠር የህብረቱ ሙሉ አባል ለመሆን ማከናወን ካለባት የቤት ስራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
27 አባላት ያሉት ሀብረቱ በሚቀጥሉት አመታት የአባላቱን ቁጥር እስከ 36 ሊያደርስ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ ለአሁኑ ግን የዩክሬን እና ሞልዶቫን አባልነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ድርድሩን በመጭው ሳምንት ማክሰኞ ይጀምራል፡፡