ዩክሬን ሞንጎሊያ ፕሬዝደንት ፑቲንን በቁጥጥር ስር እንድታውል ጠየቀች
አይሲሲ ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ስልጣን ስለሌለው በአባል ሀገራት ትብብር ላይ ጥገኛ ነው
ፑቲን አይሲሲ የእስር ማዘዣ ካወጣባቸው ወዲህ የፍርድ ቤቱ አባል ወደ ሆነች ሀገር የሚያደርጉት ይህ ጉብኝት የመጀመሪያቸው ይሆናል
ዩክሬን ሞንጎሊያ ፕሬዝደንት ፑቲንን በቁጥጥር ስር እንድታውል ጠየቀች።
ዩክሬን የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በሚቀጥለው ሳምንት ሞንጎሊያን በሚጎበኙበት ወቅት ሀገሪቱ በቁጥጥር ስር እንድታውላቸው ጠይቃለች።
ፑቲን አለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት(አይሲሲ) የእስር ማዘዣ ካወጣባቸው ወዲህ የፍርድ ቤቱ አባል ወደ ሆነች ሀገር የሚያደርጉት ይህ ጉብኝት የመጀመሪያቸው ይሆናል።
ፍርድ ቤቱ በፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ ያወጣባቸው የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የዩክሬን ህጻናትን ያለፍቃዳቸው ወደ ሩሲያ በመውሰድ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ምክንያት ነው።
የአይሲሲ ቃል አቀባይ የሞንጎሊያ ባለስልጣናት ለአይሲሲ መመሪያዎች ተገዥ የመሆን ግዴታ እንዳለባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የሩሲያ ቤተመንግስት ወይም ክሬሚሊን በሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ይካሄዳል ስለተባለው ገብኝት "የሚያስጨንቅ ነገር የለም" ብሏል። "ከሞንጎሊያ አጋሮቻቸውን ጋር እጅግ ጥሩ የሚባል መግባባት አለን" ሲሉ የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።"በእርግጥ የፕሬዝደንቱ ጉብኝት በጥንቃቄ የሚደረግ ነው።"
ፍርድ ቤቱ ፑቲንን በጦር ወንጀል ጠርጥሮ የእስር ማዘዣ ያወጣባቸው ባለፈው ሳምንት ነበር። ፍርድ ቤቱ ከፕሬዝደንቱ በተጨማሪ በሩሲያ የህጻናት መብት ኮሚሽነር ማሪያ ልቮቫ ቤሎቫ ላይም በተመሳሳይ ጉዳይ የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸው ነበር።
አይሲሲ ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ስልጣን ስለሌለው በአባል ሀገራት ትብብር ላይ ጥገኛ ነው።
ዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሞንጎሊያ "ቭላድሚር ፑቲን የጦር ወንጀለኛ መሆናቸውን" ታቃለች ብሎ ተስፋ እንደሚያደርግ ገልጾ፣ የሀገሪቱ ባለስልጣናት የሩሲያውን መሪ አስረው በዘሄግ ለሚገኘው አይሲሲ እንዲያስረክቡ ጥሪ አቅርቧል።