
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ሩሲያ ወደቦቹን በመቆጣጠሯ ምክንያት ዩክሬን በአስር ሚሊዮን ቶን የሚቆጠር እህል ልታጣ ትችላለች ብለዋል
ዩክሬን በሩሲያ ቁጥጥር ስር የገቡትን አራት የጥቁር ባህር እና የአዞቭ ወደቦችን በይፋ መዝጋቷን የዩክሬን ግብርና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የአዞቭ የባህር ወደቦችን ማለትም ማሪዮፖልን፣ ብሬዲያንስክን፣ ስካዶቭስክን እና በጥቁር ባህር የሚገኘውን የኬርሶን ወደብን “በድጋሚ መቆጣጠር እስከምንችል ድረስ” ዝግ እንዲሆኑ ተደርጓል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
"ይህ እርምጃ የተወሰደው ለመርከቦችን እና ለተሳፋሪዎችን አገልግሎት መስጠት፣ ጭነት፣ ትራንስፖርት እና ሌሎች ተያያዥ ኢኮኖሚያዊ ተግባራትን ማከናወን ባለመቻሉ እና ተገቢውን የአሳሽ ደህንነት ደረጃ በማረጋገጥ ነው" ብሏል የዩክሬን ግብርና ሚኒስቴር፡፡
በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ በሩሲያ ወረራ ምክንያት ሁሉም የዩክሬን የባህር ወደቦች እንቅስቃሴያቸውን አቁመዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ሰኞ ዕለት እንደተናገሩት ዩክሬን በአስር ሚሊዮን ቶን የሚቆጠር እህል ልታጣ ትችላለች፤ ሩሲያ በያዘችው የጥቁር ባህር መርከቦች ቁጥጥር ሳቢያ አውሮፓን፣ እስያ እና አፍሪካን የሚጎዳ የምግብ ቀውስ አስከትሏል።
"ሩሲያ መርከቦች እንዲገቡ ወይም እንዲወጡ አትፈቅድም፡፡ ጥቁር ባህርን እየተቆጣጠረች ነው" ሲል ዘሌንስኪ ለአውስትራሊያ የዜና ፕሮግራም 60 ደቂቃ ተናግሯል፡፡
"ሩሲያ የሀገራችንን ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ ማገድ ትፈልጋለች፡፡"
ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ጦርነት ዩክሬንን ትጥቅ ለማስፈታት ያለመ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ስትል ሰይማዋለች፡፡ ምእራባውያን እና ዩክሬን ሩሲያ ለጦርነቱ መቀስቀስ እንደምክንያት ያቀረበችውን አይቀበሉትም፡፡
በግብርና ምርት የምትታወቀው ዩክሬን አብዛኛውን እቃዎቿን በባህር ወደ ውጭ ትልክ ነበር፡፡ ነገርግን በምእራብ ድንበሯ አልያም በትንንሽ የዳኑቤ ወንዝ ወደቦች በባቡር ወደ ውጭ ለመላክ ተገድዳለች። ሚኒስቴሩ ባለፈው ሳምንት የዩክሬን እህል ወደ ውጭ የሚላከው በፈረንጆቹ በ2021/22፣ ከሐምሌ እስከ ሰኔ ወር 45.709 ሚሊዮን ቶን ደርሷል።
መጠኑ በሚያዝያ ወር ወደ ውጭ የተላከውን 763,000 ቶን አካቷል፤ ነገርግን ምንም ተነጻጻሪ አሃዞችን አልሰጠም ብሏል። ከፍተኛ የግብርና ባለስልጣናት በዚህ ወር ዩክሬን 300,000 ቶን እህል ወደ ውጭ ልካለች።